የሳዑዲ አረቢያ አልጋ ወራሽ የኢራኑን ከፍተኛ መሪ ከአዶልፍ ሂትለር ጋር አመሳሰሉ
የሳዑዲ አረቢያ አልጋ ወራሽ ሞሐመድ ቢን ሳልማን የኢራኑን ከፍተኛ መሪ ከአዶልፍ ሂትለር ጋር አመሳስለዋል። ኢራን የኑክሌር ቦምብ ከሰራች ሳዑዲ አረቢያም በፍጥነት ኑክሌር ትስራለች ሲሉም ዝተዋል።
ዋሺንግተን ዲሲ — የሳዑዲ አረቢያ አልጋ ወራሽ ሞሐመድ ቢን ሳልማን የኢራኑን ከፍተኛ መሪ ከአዶልፍ ሂትለር ጋር አመሳስለዋል። ኢራን የኑክሌር ቦምብ ከሰራች ሳዑዲ አረቢያም በፍጥነት ኑክሌር ትስራለች ሲሉም ዝተዋል።
“ሳዑዲ አረቢያ ኑክሌር ቦምብ እንዲኖራት አትፈልግም፣ ኢራን ከሰራች ግን በፍጥነት ፈለጓን እንደምንከተል አይጠራጥርም” ሲሉ የሳዑዲ አረቢያው አልጋ ወራሽ በአንድ የአሜሪካ ቴሌቪዥን በተደረገላቸው ቃልመጠይቅ ተናግረዋል።
የሠላሳ ሁለት ዓመት ዕድሜው አልጋ ወራሽ የኢራኑን ከፍተኛ መሪ አሊኻሚኒን አያያዝ በናዚ ጀርመን አነሳስ ወቅት ከነበረው የሂተለር አያያዝ ጋር አመሳስለዋል።
ሂትለር ባዛን ወቅት ሊያሰፋው እንደፈለገው ዕምነቱ ሁሉ አሊኾሚኒም በመካከለኛው ምሥራቅ የራሳቸውን ውጥን ለመፍጠር ይፍልጋሉ ብለዋል።
Share your thoughts on this post