fbpx

የሰኔ 16ቱ ሰልፍ ላይ የቦንብ ጥቃት ያቀነባበሩና የመሩ ተለይተው መታወቃቸው እየተገለፀ ነው

እየወጡ ያሉ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ከሆነ !

ባለፈው ቅዳሜ ሰኔ 16 ቀን 2010 ዓ.ም በአዲስ አበባ አብዮት አደባባይ ዶ/ር አብይን ለመደገፍ በተካሄደው ህዝባዊ ትህይንት ላይ የደረሰውን የቦንብ ጥቃት ያቀነባበሩና የመሩ ተለይተው መታወቃቸው እየተገለፀ ነው።

በዚህ የቦንብ ጥቃት ምርመራ ላይ የአሜሪካዊ FBI እና CIA ፣ የእስራኤል MOSAD እንዲሁም የእንግሊዙ የስለላ ድርጅት NCIA የተሳተፉበት ጭምር ነው። በዓለም አቀፍ የስለላ ድርጅቶቹ ተጠንቶ የሚቀረበው የወንጀል ምርመራ የተጠበቀ እና ያልተጠበቀ ውጤቶችን ይፋ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል። ከዚሁ ጋር በተያዘ አቶ ዘይኑ ጀማል የፌዴራል ፖሊስ ዋና ኮሚሽነር የወንጀሉ ምርመራ መጠናቀቁ ከትላንት በስቲያ መግለጻቸው የሚታወቅ ነው።

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram