fbpx

የሰሜን ኮሪያ ጀነራል ተጨማሪ ምግብ ለጓደኛው በመስጠቱ በሞት ተቀጣ

የሰሜን ኮሪያው ፕሬዚዳንት ኪም ጁንግ ኡን አንድ ከፍተኛ ወታደራዊ ባለስልጣን ተጨማሪ ምግብ ለጓደኛቸው በመስጠቱ ምክንያት በሞት መቅጣታቸው ተነገረ፡፡

የ56 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ጁ ሶንግ የተባሉት ግለሰብ በኮሪያ ጦር ውስጥ በሌተናል ጀነራልነት ማዕረግ እያገለገሉ እንደነበር ተጠቅሷል፡፡

ሶሃ ሳተላይት ማምጠቂያ ማዕከል ለሚሰራ ጓደኛቸው ለቤተሰቦቹና ለወታደሮቹ የሚሆን የተጨማሪ ሩዝና በቆሎ ራሽን ነው የሰጡት ተብሏል፡፡

በኪም ያልጸደቀ 590 ኪሎ ግራም ሩዝ፣ 730 ኪሎ ግራም በቆሎ እና 900 ኪሎ ግራም ነዳጅ ነው ያስተላለፉት፡፡

ይህንንም ተከትሎ ኃላፊው ስልጣናቸውን ያለአግባብ ተጠቅመዋል እንዲሁም ከፓርቲው ተጻራሪ በሆነ መንገድ ቆመዋል በሚል ወንጀል ለመከሰስ በቅተዋል፡፡

በዚህም ፕዮንግያንግ በሚገኝ ወታደራዊ ጣቢያ ውስጥ በዘጠኝ ወታደሮች አማካኝነት በ90 ጥይት ተደብድበው መገደላቸው ተገልጿል፡፡

ኪም ከዚህ ቀደምም የመከላከያ ሚኒስትራቸውን በስብሰባ ወቅት እንቅልፍ ተኝተኻል በማለት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በተሰበሰቡበት እንዲገደሉ ማዘዛቸው የሚታወስ ነው፡፡

 

 

ምንጭ፦ኤምኤስኤን

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram