fbpx

የሰሜን ኮሪያና የአሜሪካ መሪዎች ስብሳባ እስኪጠናቀቅ ሲንጋፖር በአየር በረራ ላይ ገደብ ልትጥል ነው

በሚቀጥለው ሳምንት የአሜሪካና የሰሜን ኮሪያ መሪዎች በሲንጋፖር በሚያካሂዱት ስብሰባ ወቅት ሲንጋፖር በአየር በረራ ላይ ገደብ ልትጥል መሆኑ ተገልጿል።

በዚሁ ፕሮግራም ወቅት ከሌሎች አካባቢዎች ወደ ሲንጋፖርና ከሲንጋፖር ወደ ሌሎች አካባቢዎች የሚጓዙ መንገደኖች ፕሮግራማቸውን ማራዘም እንዳለባቸው የሲንጋፖር የመከላከያና የሲቪል አቪዮሽን ባለስልጣናት ገልጸዋል ተብሏል።

ለደህንነት ቁጥጥር ሲባልም በዚህ ወቅት በሲንጋፖር ቻንጊ የአየር ማረፊያ የሚያርፉ አውሮፕላኖች ፍጥነት እንዲቀንሱና በወቅቱ የሚወጡ የበራረ ገደቦችን እንዲያከብሩ ትዕዛዝ መተላለፉም ነው የተገለጸው።

ዓለም አቀፉ የሲቪል አቪዎሽን ድርጅት በበኩሉ የሁለቱ መሪዎች ስብሰባ እስኪጠናቀቅ ፓያ ለባር የጦር ሰፈር ከማንኛውም ወታደራዊ እንቅስቃሴ የጸዳ መሆን እንዳለበት አስጠንቅቋል ተብሏል።

በዚህም ፕሬዚዳንት ትራምፕና ኪም ጆን ኡን በፈረንጆቹ ሰኔ 12 በደቡብ እስያዋ ከተማ ለሚካሂዱት ታሪካዊ ስብሰባ የደህንነት ጥበቃ ስራዎች እየተጠናከሩ መሆኑ ነው የተገለጸው።

የሁለቱ መሪዎች ስብሰባም በሲንጋፖር ደቡባዊ አካባቢ በምትገኘው ሰንቶሳ ደሴት ሊካሄድ የታቀደ ሲሆን፥ ሲንጋፖር ለዚሁ ፕሮግራም ከፈረንጆቹ ሰኔ 10 እስከ 14 ቅድመ ሁኔታዎችን አዘጋጅታ እየተጠባበቀች መሆኑን ዘገባው አመላክቷል።

በዚሁ አካባቢ ስብሰባው እስከሚጠናቀቅ ድረስ በረጅም ርቀት ቁጥጥር የሚበሩ አውሮፕላኖችና ማንኛውም የኤሌክትርኒክስ መገናኛ መሳሪዎች አገልግሎት ላይ ማዋል እንደማይቻል ዘገባው ያስረዳል።

 

 

 

ምንጭ፦ reuters.com

 

የተተረጎመው፦ በእንቻለው ታደሰ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram