fbpx

የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ አሳዳሪዎች በሚሊየን የሚቆጠሩ የትዊትር ተከታዮችን ማጣታቸው ተገለጸ

ትዊተር የብዙ ደንበኞቹን የትዊተር አገልግሎት ማቋረጡን ተከትሎ የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዚዳንትን ጨምሮ በርካታ ታላላቅ ሰዎች ብዙ ተከታዮችን ማጣታቸው ተነገረ፡፡

ትዊተር ባለፈው ሳምንት በሁለት ወራት ጊዜ ውስጥ ብቻ ከ70 ሚሊየን በላይ የትዊተር አካውንቶችን ማገዱ ይታወሳል፡፡

የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ከእግዱ በፊት ከ103 ሚሊየን ተከታይ በላይ የነበራቸው ሲሆን፥ ሰሞኑን 2 ሚሊየን ተከታዮችን በማጣት ወደ 101 ሚሊየን አሽቆልቁሎባቸዋል፡፡

የአሁኑ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ደግሞ 340 ሺህ ተከታዮችን ያጡ ሲሆን፥ በጥቅሉ 53 ሚሊየን የትዊትር ተከታዮችን አፍርተዋል፡፡

በትዊተር ተከታዮች ብዛት ታዊቂ የሆነችው አቀንቃኝ ኬቲይ ፔሪይ 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ተከታዮቿን ያጣች ሲሆን ወደ 107 ሚሊየን ተከታዮች እንደወረደባት ተገልጿል፡፡

እንዲሁም ጀስቲን ቢበርና ታይለር ስዊፍት እያንዳንዳቸው 2 ሚሊየን ተከታዮችን በማጣት ወደ 104 ሚሊየን እን 83 ሚሊየን ተከታዮች ላይ መቀመጣቸው ተነግሮዋል፡፡

ኩባንያው የደንበኞቹን አገልግሎት ያቋረጠው በማህበራዊ ሚዲያው የሚዘዋወሩ የተዛቡ መረጃዎችን ለመቀነስ አስቦ መሆኑ እየተነገረ ነው፡፡

 

ትዊተር 336 ሚሊየን ያህል ደንበኞች ያሉት ሲሆን፥ ከነዚህም መካከል 70 ሚሊየን ያህሉን ወይንም ስድስት በመቶውን ቀንሷል፡፡

በዚህም ባለፉት ሁለት ወራት በየዕለቱ አንድ ሚሊየን ያህል ደንበኞቹን አገልግሎት ማቋረጡን ገልጾ፥ ይህንኑ ተግባር እስከ ነሃሴ ወር ድረስ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስታውቋል፡፡

 

ምንጭ፦ታይም
በአብርሃም ፈቀደ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram