fbpx

የመጀመሪያው ሰው ሰራሽ ‘‘አይሪስ’’ የተባለው የዓይን ክፍል ይፋ ሆነ

የመጀመሪው ሰው ሰራሽ ‘‘አይሪስ’’ የተባለው የአይን ክፍል ይፋ መሆኑን የአሜሪካ የምግብና መድሃኒት አስተዳደር አረጋግጧል።

የአሜሪካ የምግብና መድሃኒት አስተዳደር ለዚሁ ቴክኖሎጂ እውቀና የሰጠውም በ389 ያህል ሰዎች ላይ ስኬታማ የህክምና ውጤት ከታየ በኋላ ነው ተብሏል።

ህክምናው ከተደረገላቸው ሰዎች መካከል 70 በመቶ ያህሉ እይታቸው ላይ ቀደም ሲል ተከስቶ የነበረው ችግር የተቃለለ መሆነኑን ሲያስረዱ 94 በመቶ ያህሉ ደግሞ በአይናቸው ላይ የነበረ ጠባሳ መወገድና በሰውሰራሹ ‘‘አይሪስ’’ መተካት መቻሉ ምቾት የሰጣቸው መሁኑን ማስረዳታቸውን ነው የተገለጸው።

ሰው ሰራሽ ‘‘አይሪሱ’’ ስስ፣ በቀላሉ የሚተጣጠፍና የተጠቃሚዎቹን የአይን መጠን፣ የቀለም ልዩነትን እና ምርጫ ታሳቢ አድርጎ የተሰራ መሆኑም ነው የተገለጸው።

አዲሱ ቴክኖሎጂ በተለያዩ አዳጋዎች አይናቸው ላይ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎችን ችግር በቀዶ ህክምና ለማስተካከል ማስቻሉም ነው የተመላከተው።

የአሜሪካ ምግብና መድሃኒት አስተዳደር ቴክኖሎጂውን ነፍሰጡር እናቶች መጠቀም እንደሌለባቸው የሳሰበ ሲሆን፥ ሌሎች ተደራራቢ የአይን ችግሮች ያሉባቸው የአይን ህሙማንም እነዚህን ችግሮች ከማስተካከል በፊት ይህንን ቴክኖሎጂ መጠቀም እንደሌለባቸው እስረድቷል።

 

 

 

 

ምንጭ፦ upi.com

የተተረጎመው፦ በእንቻለው

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram