fbpx

ዛሬ ምሽት ሊቨርፑልና ሪያል ማድሪድ ለቻምፒየንስ ሊግ ፍጻሜ ይፋለማሉ

በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ፍጻሜ ውድድር ዛሬ ምሽት ሊቨርፑልና ሪያል ማድሪድ ኬቭ ላይ ይፋለማሉ፡፡

የቻምፒየንስ ሊግ ፍጻሜን ውድድር ለመከታተል ደጋፊዎች በዩክሬን ዋና ከተማ ኬቭ መከተማቸው ተነግሯል፡፡

የዘንድሮውን የቻምፒየንስ ሊግ ውድድር ሪያል ማድሪድ የሚያነሳ ከሆነ ለአስራ ሶስተኛ ጊዜ ሲሆን፥ እንዲሁም ለሶስት ተከታታይ ዓመታት ለማሸነፍ ነው የሚፋለመው፡፡

ሊቨርፑል ዋንጫውን የሚያነሳ ከሆነ ደግሞ በታሪኩ ለስድስተኛ ጊዜ ያነሳ ተብሎ ታሪክ ይጻፍለታል፡፡

ጀርመናዊው የሊቨርፑል አሰልጣኝ ጀርገን ክሎፕ እና ፈረንሳያዊው የሪያል ማድሪድ አሰልጣኝ ዚነዲን ዚዳን ለውድድሩ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

ከዚህ ቀደም ክሎፕ አንድ ጊዜ ለቻምፒየንስ ሊግ ፍጻሜ የደረሰ ሲሆን፥ ዚዳን በአንጻሩ በተጫዋችነትም በአሰልጣኝነትም የቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫን አንስቷል፡፡

በዛሬው ጨዋታ በሀገሩ ግብጽ ጎዳናና ትምህርት ቤት የተሰየመለት ሳላህና አራት ጊዜ ባሎንዶርን የበላው ሮናልዶ ዋነኛ ተጠባቂዎች ናቸው፡፡

ሳላህ በክለቡ በተወዳደረባቸው የ2017/18 ሁሉም ጨዋታዎች 49 ጎል ያስቆጠረ ሲሆን፥ ሮናልዶ ደግሞ 41 ግቦችን አስቆጥሯል፡፡

በቻምፕየንስ ሊግ የእስከአሁን ጉዞ ደግሞ ሳላህ 11 ሲያገባ አራት ለጎል የሚሆኑ ኳሶችን አቀብሏል፡፡

ሮናልዶ ደግሞ 15 ግቦችን አስቆጥራል እንዲሁም ሁለት ለግብ የሚሆን ኳሶችን አቀብሏል፡፡

ሊቨርፑልን ሮማን ማድሪድ ባየር ሙኒክን በደርሶ መልስ ውጤት አሸንፈው ነው ለዛሬው የፍጻሜ ውድድር የበቁት፡፡

ሊቨርፑልና ማድሪድ ዛሬ ለፍጻሜ የሚወዳደሩበት ስታዲየም በምስራቅ አውሮፓ ሁለተኛውና ትልቁ ነው የተባለለት ሲሆን፥ ከ63 ሺህ በላይ ሰዎችን ይይዛል ተብሏል፡፡

የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫን ስፔን 17 ጊዜ፣ እንግሊዝና ጣሊያን እያንዳዳቸው 12 ጊዜ አንስተዋል፡፡

የፍጻሜ ውድድሩ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር 3፡45 ላይ ይታያል፡፡

ምንጭ፥ስካይና ቴሌግራፍ
በአብርሃም ፈቀደ ወደ አማርኛ ተመለሰ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram