ዚምባቡዌ በሐምሌ 23 ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ እንደምታካሄድ ይፋ አደረገች

የዚምባቡዌ ፕሬዚዳንት ኤመርሰን ማናንጋጓ ሀገራቸው በሐምሌ 23 ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ እንደምታካሄድ አስታወቁ፡፡

ይህ ምርጫ ከ 30 ዓመታት በኃላ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤ በሌሉበት የሚደረግ የመጀመሪያው መርሃ-ግብር ነው፡፡

ማናንጋጓ በህዳር ወር በወታደሩ በመታገዝ ነበር ወደ ስልጣን የመጡት፡፡

ማንንጋጓ በምርጫው የሚሳተፉ ሲሆን ተፎካካሪያቸው የ40 ዓመቱ ኔልሰን ቻሚሳ ናቸው ተብሏል፡፡

ኔልሰን ቻሚሳ በዚህ ዓመት በሞት የተለዩት የሞርጋን የቻንጋራይ ተተኪ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

እስከአሁን ድረስ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ያለምንም እስራትና ዛቻ የምርጫ ቅስቀሳቸውን በማካሄድ ላይ ናቸው ተብሏል፡፡

በፕሬዚዳንታዊ ውድድሩ አሸናፊ የማይኖር ከሆነ በመስከረም መጀመሪያ ዳግም ምርጫ እንደሚደረግ ፕሬዚዳንቱ በመግለጫቸው አንስተዋል፡፡

 

 

ምንጭ፦ አልጀዚራ
በአብርሃም ፈቀደ ወደ አማርኛ ተመለሰ

Share your thoughts on this post

Advertisements
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram