ዓለም አቀፉ ጣናን መልሶ ማቋቋም ህብረት ያስመጣው የእንቦጭ ማስወገጃ ማሽን ስራ ጀመረ

የዓለም አቀፉ ጣናን መልሶ ማቋቋም ህብረት የሳይንቲፊክ ቡድን መሪውን ዶክተር ይሁን ድሌ ዛሬ በጣና ሀይቅ ተገኝተው ማሽኑን ስራ አስጀምረዋል፡፡

ማሽኑም በሀይቁ ላይ ያለምንም ችግር ስራውን ሲከውን ውሏል፡፡
ህብረቱ በቀጣይም ተጨማሪ ማሽኖችን ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት ዝግጅት ላይ ሲሆን የአቅም ግንባታ ስልጠና በመስጠት ሚናውን እንደሚያጎላ ተነግሯል፡፡

ዛሬ በጣና ሀይቅ ላይ እንቦጭ የማስወገድ ስራውን የጀመረው ማሽን ከሰሞኑ ወደ ሀገር ቤት የገባ ማሽን ነው፡፡

67 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ወጭ የሆነበት ሲሆን በማጓጓዙ ሂደት የኢትዮጵያ መርከብ ድርጅት እና ጥቁር አባይ ትራንስፖርት ድርጅት ተሳታፊዎች ናቸው፡፡
ህብረቱም የአማራ ክልል መንግስትንና በሂደቱ የተሳተፉትን በሙሉ አመስግኗል፡፡

ምንጭ፡- አብመድ

Share your thoughts on this post

%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram