fbpx
AMHARICPOLITICSWORLD

ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት እኔን የመጠየቅ መብት የለውም – የፊሊፒንሱ ፕሬዚዳንት

የፊሊፒስ ፕሬዚዳንት ሮድሪጎ ዱቴርቴ ወደ ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት (አይሲሲ) ለመቅረብ የሚያበቃቸው ወንጀል እንዳልሰሩ ተናገሩ።

ዱቴርቴ ከ19 ወራት በፊት በአደንዛዥ እፅ ዝውውር ላይ በከፈቱት ዘመቻ ምክንያት ለጠፋው የሰው ህይወት ሊጠየቁ ይገባል ሲሉ የሀገሪቱ የህግ ባለሙያዎች መጠየቃቸውን ተከትሎ ነው ይህን ያሉት።

ዱቴርቴ በበኩላቸው ስለአይሲሲ ሲናገሩ “በሚሊየን ዓመት ውስጥም ቢሆን እኔን ፍርድ ቤት አያቆመኝም“ ብለዋል።

ጨምረውም ድርጅቱ “ጥቅም አልባ” እና “ግብዝ” ነው ሲሉ አስተያታቸውን ሰንዝረዋል።

የፕሬዚዳንቱ ቃል-አቀባይ በዕጽ ላይ የተከፈተው ዘመቻ በሰብዓዊነት ላይ የተፈጸመ ወንጀል አድርጎ መውስድ አይቻልም ብለዋል።

ፖሊስ እስካሁን ከ4 ሺህ የሚበልጡ የአደንዛዥ ዕፅ አዘዋዋሪዎችን መግደሉ ይነገራል።

ዱቴርቴ በዓለም አቀፍ ደረጃ አይሲሲን በተመለከተ ያጸደቀቸውን የሮም ስምምንት ምናልባትም አገራቸው እንደማትቀበል ነው የገለፁት።

ምክንያታቸው ደግሞ በይፋዊ መንገድ በጋዜጣ ባለመታወጁ ነው ብለዋል።

ምንጭ፦ ሮይተርስ
ተተርጉሞ የተጫነው፦ አብረሃም ፈቀደ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram