fbpx

ውሃ እንደሚሞት ያውቃሉ?

ውሃ ለምድር አስፈላጊ ከሆኑ ነገሮች መካከል ዋነኛው ነው ዓለምን ያለውሃ ማሰብ ከቶም አይቻልም፡፡

ውሃ በዓለም ላይ ለሰው ልጆች ስጋዊም መንፈሳዊም ድህነቶችን እንደሚሰጥ እሙን ነው፡፡

በኛዋ ፀሐይ ምህዋር ከሚገኙ ፕላኔቶች መካከልም ውሃ የምትገኘው በምድር ላይ ብቻ ነው፡፡

ታዲያ በምድር ላይ በየውቅያኖሱ፣ በየወንዙ እንዲሁም በየሐይቅ ላይ የሚገኘው ውሃ እንዴት ሊሞት ይችላል፡፡

ነገሩ ወዲህ ነው በዚህ ሳምንት በብሪታንያ ማንቸስተር ዩኒቨርስቲ ውስጥ በተሰራ ጥናት ውሃ እንደሚሞት አረጋግጠዋል፡፡

ይህም የሆነው ውሃ በባህሪው ኤሌክትሪክ አስተላላፊ እነደመሆኑ መጠን ሞቷል የሚባለው ውሃ በአንጻሩ የኤሌክትሪክ ፍሰት አይኖረውም ተብሏል፡፡

ተመራማሪዎቹ ሞቷል ያሉት ውሃ ለምን ኤሌክትሪክ እንደማያስተላልፍ ምክንያቱን ሲያስረዱ እንዲህ ብለዋል፡፡

በውሃ ውስጥ የሚገኙት ሞለኪዩሎች ሲሳሱ ወይንም ወደ ጠጣርነት ሲቃረቡ ኤሌክትሪክ ማስተላለፍ ያቆማሉ ብለዋል፡፡

ይህንንም ተከትሎ ነው ተመራማሪዎቹ በኤሌክትሪካዊ አካሄድ ውሃ ሙት መሆኑን አረጋግጠናል ያሉት፡፡

 

 

ምንጭ ሳይንስ ዴይሊይ
በአብርሃም ፈቀደ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram