fbpx

ወደ አሶሳ ያቀናው የሐኪሞች ቡድን ለተጎጂዎች የህክምና አገልግሎት ሰጠ

ወደ አሶሳ ያቀናው ከፍተኛ የሀኪሞች ቡድን ሰሞኑን በከተማው ተከስቶ በነበረው ግጭት ለተጎዱ ነዋሪዎች ቀዶ ህክምና አካሄደ፡፡

እስከአሁን 13 ግለሰቦች በተሳካ ሁኔታ ቀዶ ህክምና እንደተደረገላቸው የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ዶክተር አሚር አማን አስታውቀዋል፡፡

እንዲሁም በአሁኑ ሰዓት አራት ግለሰቦች ደግሞ የቀዶ ህክምና እየተሰጣቸው መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

በዶክተር ብርሀኑ ነጋ አለሙ የተመራዉ ከጥቁር አንበሳ ሆሰፒታል እና ከቅዱሰ ጳዉሎስ ሆስፒታል የተውጣጡ 14 ከፍተኛ የሀኪሞች ቡድን ወደ አሶሳ ያቀናው አርብ ዕለት እንደነበር ይታወሳል፡፡

ኤፍ.ቢ.ሲ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram