fbpx

ኬንያ እጃቸውን በሙስና ቅሌት አስገብተዋል ያለቻቸውን ሀላፊዎች በስር ቁጥጥር ማዋል ጀመረች

ኬንያ እጃቸውን በሙስና ቅሌት አስገብተዋል ያለቻቸውን ሀላፊዎች በስር ቁጥጥር ማዋል ጀመረች፡፡
78 ሚሊዮን ዶላር መዝብረዋል ያለችውን ሀላፊ በቁጥጥር ስር በማዋል ከ40 በላይ ሃላፊዎች ላይ ክስ መስርታች፡፡

የኬንያ ፖሊሶች 8 ቢሊየን ሺሊንግ ወይም 78 ሚሊዮን ዶላር ሙስና ፈፀሙ የተባሉትን የሀገሪቱ ወጣቶች ድርጅት ዋና ዳይሬክተሩን በቁጥጥር ስር አውሎታል።

ብሔራዊ የወጣት አገልግሎት (ኒውስ) ዋና ዳይሬክተር ሪቻርድ ኑዱቤን በቁጥጥር ሥር የዋሉ ሲሆኑ 40 ሲቪል ሰርቪስ እና 14 የግል ባለሥልጣናትም ክስ ተመስርቶባቸዋል።
ባለፉት ሶስት ዓመታት ውስጥ ብሄራዊ የወጣቶች አገልግሎት ድርጅት ላይ የተፈፀመ ሁለተኛው የሙስና ወንጀል ነው በተባለለት በዚህ ድርጊት በሙስና በተጠረጠሩት ውስጥ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት እና የውጭ አምራቾች እጅ እንዳለበት ተገልጿል።

የኬንያ ዋና አቃቤ ህግ ኖርዲን ሞሃመድ ሀጂ በባንኩ የቢዝነስ ጉባኤ እንደገለጹት ባንኮችንና በቢሮ ውስጥ ያለውን ሚና እንደሚመረምር ለሮይተርስ ገልፀዋል።
ይህ ምርመራ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ እ.ኤ.አ. በ 2013 ለመጀመሪያ ጊዜ በተመረጡበት ጊዜ ሙስናን ለማስወገድ ቃል መግባታቸውን ተከትሎ የተተገበረ እንደሆነ ይታመናል።

ለብሄራዊ ወጣቶች አገልግሎት ድርጅት የተሰጠው በጀት በኬንያ ያለውን ከፍተኛ የወጣቶች ሥራ አጥነት ለመቀየር፤ የወጣቶችን ህይወት እና የንግድ ስራ ክህሎቶችን ለማሰልጠን የሚያስችሉ ትግበራዎች ውስጥ አንዱ የፕሬዚዳንት ኡህሩ ኬንያታ እቅድ አካል ነው።

በሙስና የተካፈሉ አቅራቢዎች ያቀረቧቸው የሙስና ቅሌቶች በኒ.ኤም.ኤስ አማካኝነት በተለመዱ ደረሰኞች እና በበርካታ ክፍያዎች የተሰረዙ ገንዘቦችን ተመልክተዋል።
የኬንያ ብሄራዊ የወጣቶች አገልግሎትን ጨምሮ ብሔራዊ የሰብሎች እና ምርቶች ቢሮ እና ባልተገለፁ ተቋማት ላይ ክስ እንደሚመሰርት የኪንያ የህዝብ ቅሬታ ሰሚ ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።

በኬንያ ሙስና እጅግ አስነዋሪ ቅሌትነቱ እስከአሁን ቀጥሏል። የሃገሪቱ ዋና ኦዲተር መስርያ ቤት በመጋቢት ወር ባወጣው ሪፖርት በሃገሪቱ እስከአሁን በሙስና 400 ሚሊዮን ዶላር የመንግስት ገንዘብ መመዝበሩን አስታውቋል።

በቅርብ ሣምንት ውስጥ ብቻ እንኳ 30 ሚሊየን ዶላር የተጭበረበሩ ክፍያዎች በብሔራዊ የሰብሎች እና ምርቶች ቦርድ (NCPB) ላይ ተገኝተዋል።

በተጨማሪም በዚሁ የኬንያ የኤሌክትሪክ ሃይል ማከፋፈያ ኩባንያ ሃላፊ ለጓደኞቻቸውና ለቤተሰቦቻቸው የብዙ ሚሊዮን ዶላር ኮንትራት መሰጠቱን የተገኙ መረጃዎች ያሳያሉ ተብሏል።

ምንጭ፡-ቢቢሲ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram