fbpx

ኬንያ ህጋዊ መረጃ ያልያዙ ስደተኞች እንዲመዘገቡ ወይንም ከሀገር እንዲወጡ 60 ቀናትን ሰጠች

የምስራቅ አፍሪካዋ ኬንያ በሀገሯ የሚገኙ ስደተኞች ለመቆጣጠር እንዲያመቻት ቀርበው ምዝገባ እንዲያደርጉ ወይንም ከሀገር እንዲወጡ 60 ቀናት መስጠቷን አስታወቀች፡፡

የሀገሪቷ የአገር ውስጥ ሚኒስትር ፍሬድ ማቲያንግእ ህጋዊ መረጃ ያልያዙ ስደተኞች የጸጥታ ስጋት መሆናቸውንና እንዲሁም ግብር እንደማይከፍሉ እና የዜጎችን የስራ እድል እንደሚነጥቁ ገልጸዋል፡፡

በተሰጣቸው የጊዜ ገደብ ወስጥ የማይመዘገቡ ስደተኞች ወደ እስር እንደሚወርዱ አሳስበዋል፡፡

በሀገሪቷ ከ100 ሺህ በላይ ስደተኛ እንደሚኖር ያስታወቁት ሚኒስትሩ ከነዚህ መካከል 34 ሺህ የሚያህሉት ብቻ ናቸው የስራ ፍቃድ ያላቸው ብለዋል፡፡

ሚኒስትሩ ኬንያ ስደተኞችን ወደ መጡበት ሀገር ለመመለስ ለአየር ትኬት በየዓመቱ 3 ነጥብ 6 ሚሊየን ዶላር እንደምታወጣ ገልጸዋል፡፡

ምንጭ፦ሲጂቲኤን

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram