ካናዳ 13 ቢሊየን በሚያወጡ የአሜሪካ ምርቶች ላይ ቀረጥ ጣለች

ካናዳ 12 ነጥብ አምስት ቢሊየን በሚያወጡ ወደ ሀገርዋ በሚገቡ የዩናይትድ ስቴትስ ምርቶች ላይ ቀረጥ መጣሏን አስታወቀች፡፡

ግንቦት መጨረሻ ላይ የዩናይትድ ስቴትስ መንግስት አልሙኒየም ላይ የ25 በመቶ እንዲሁም የብረት ምርቶች ላይ የ10 በመቶ ቀረጥ መጣሉ የሚታወስ ነው፡፡

አብዛኛው ወደ የዩናይትድ ስቴትስ ከሚገባው ምርት ውስጥ ካናዳ ትልቁን ድርሻ የምትወስድ ሲሆን በዚህም ክፉኛ ተጎድታለች ተብሏል፡፡

ይህንን ተከትሎ ታዲያ ካናዳ በምላሹ ቀረጥ እንደምትጥል አስታውቃ የነበረ ሲሆን፥ ትላንት 40 በሚደርሱ የብረት ምርቶች ላይ የ25 በመቶ ቀረጥና ከ80 በላይ የተለያዩ ምርቶች ላይ የ10 በመቶ ቀረጥ መጣሏን ይፋ አድርጋለች፡፡

የዩናይትድ ስቴተስ በተለያዩ ሀገራት ላይ የጣለችውን ቀረጥ ተከትሎ ሀገራት ህጋዊ እርምጃ ለመውሰድ ጉዳያቸውን ይዘው ወደ ዓለም አቀፉ የንግድ ድርጅት መሄዳቸው ይታወሳል፡፡

የአውሮፓ ህብረት ባለፈው ሳምንት ከዩናይትድ ስቴትስ በሚገቡ በሞተር ሳይክል፣ በብርትኳን ጭማቂ፣ በለውዝ ቅቤ፣ በሲጋራና በሌሎች ምርቶች ላይ የ25 በመቶ ቀረጥ ጥሏል፡፡

 

ምንጭ፦ሲኤንኤን
በአብርሃም ፈቀደ

Share your thoughts on this post

%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram