fbpx

ካርሎ ኮታሬሊ የጣሊያን ጊዜያዊ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ

የቀድሞ የአለም አቀፍ ገንዘብ ተቋም ሀላፊ የነበሩት ካርሎ ኮታሬሊ የጣሊያን ጊዜያዊ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ሰርጊዮ ማታሬላ ተሾሙ።

ካርሎ ኮታሬሊ መንግስት ለተለያዩ አገልግሎት የሚያወጣውን ወጪ እንዲቀንስ በማድረጋቸው በጣሊያኖች ዘንድ ቆራጩ የተሰኘ ቅፅል ስም ተሰጥቷቸዋል።

በጣሊያን በርካታ ወንበር ያላቸው ፋይቭ ስታር እና ዘ ሊግ ጥምር መንግስት ለመመስረት ያደረጉት ድርድር ውጤታማ ሳይሆን መቅረቱን ተከትሎ ነው ካርሎ ኮታሬሊ ጊዜያዊ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው የተሾሙት።

ይህ ሹመት ጊዜያው እንደሆነ የተጠቀሰ ሲሆን፥ በቀጣይ አመት መጀመሪያ አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር እንደሚመረጥ ታውቋል።

በቅርቡ በፋይቭ ስታር እና ዘ ሊግ ፓርቲዎች ድጋፍ ያላቸው የ81 ዓመቱ ሶቫና በፋይናስ ሚኒስትርነት ለእጩነት ቢቀርቡም የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ሳያፀድቁ መቅረታቸው ቅሬታዎች መፈጠራቸው ይታወሳል።

ጣሊያን በአውሮፓ አራተኛው ግዙፍ የኢኮኖሚ ባለቤት ስትሆን ባለፈው መጋቢት ወር በተካሄደው አጠቃላይ ምርጫ መንግስት ለመመስረት የሚያስችል መቀመጫ ያገኘ ፓርቲ ባለመኖሩ ከመጋቢት ወር ጀምር ያለ ጠቅላይ ሚኒስትር ቆይታለች።

ምንጭ፦ቢቢሲ እና ዘጋርዲያን

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram