ከ9 ዓመታት በፊት ሞቷል ተብሎ ሙሾ የተወረደለትና ተዝካሩ የወጣለት ግለሰብ በእድሜ ልክ ጽኑ እስራት ተቀጣ
ከ9 ዓመታት በፊት ሞቷል ተብሎ ሙሾ የተወረደለትና ተዝካሩ የወጣለት ግለሰብ በእድሜ ልክ ጽኑ እስራት ተቀጣ- 20 ዓመት የተፈረደባት ባለቤቱም የእውነት ጸሀይ ወጥቶላታል፡፡
ወይዘሮ ሰቀቀን አመሸ ከባለቤታቸው ከአቶ ታከለ ጥላሁን ጋር ትዳር መስርተው ጎጆ ቀልሰው በሜጫ ወረዳ -ስራ በተግባር እየተባለ በሚጠራው ቀበሌ ውስጥ ይኖሩ ነበር፡፡ በአካባቢው ማህበረሰብ ዘንድ ምስጉን የትዳር አጋሮችም ነበሩ፡፡ ሆኖም ከዛሬ 9 ዓመት በፊት መነሻው ባልታወቀ ምክንያት አቶ ጥላሁን ታከለ በባለቤታቸው እንደተገደሉ የአካባቢው ማህበረሰብ መረጃ ደረሰው፡፡ የመኖሪያ ቤታቸው በእሳት ተቃጥሎ እና 3 ልጆቻቸው በቃጠሎው ህይወታቸው ማለፉ ተረጋገጠ፡፡
አቶ ታከለ ጥላሁንም ሞተዋል ተብለው ሙሾ ወርዶላቸው ከ3 ልጆቻቸው ጋር የቀብር ስነ-ስርዓታቸው ተፈጸመ፡፡
ባለቤታቸው ወይዘሮ ሰቀቀን አመሸም በባለቤታቸው ና በልጆቻቸው ገዳይነት ተከሰው 20 ዓመት ተፈርዶባቸው ባህር ዳር ማረሚያ ቤት ቅጣታቸውን በመፈጸም ላይ እንዳሉ ከ7 ዓመታት የማረሚያ ቤት እስር በኋላ በይቅርታ ተለቀቁ፡፡
ባለቤታቸው ወይዘሮ ሰቀቀን አመሸም በባለቤታቸው ና በልጆቻቸው ገዳይነት ተከሰው 20 ዓመት ተፈርዶባቸው ባህር ዳር ማረሚያ ቤት ቅጣታቸውን በመፈጸም ላይ እንዳሉ ከ7 ዓመታት የማረሚያ ቤት እስር በኋላ በይቅርታ ተለቀቁ፡፡
ወትሮም ባለቤቴንም ልጆቼንም እኔ አልገደልኩትም ብለው ይግባኝ ብለው ሲጮሁ ማንም ያልሰማቸው ፍትህ ፈላጊዋ ወይዘሮ ሰቀቀን ከእስር እንደወጡ በሀሰት የቀብር ስን-ሰርዓት የተፈጸመለት ባለቤታቸውን ማፈላለግ ይጀምራሉ፡፡ የልጆቻቸው በእሳት ቃጠሎ መሞት በወቅቱ ተረጋግጦ ነበር፡፡
ተስፋ ያልቆረጡት ወይዘሮ ሰቀቀን እረ የፍትህ ያለህ እኔ ባሌን አልገደልኩም ብለው ሰሚ ባያገኙም ሞቶ ሙሾ የወረደለት የ67 ዓመቱ አቶ ታከለ ጥላሁንን በማፈላለግ በኦሮምያ ክልል በአንድ ቤተክርስትያን ውስጥ የጥበቃ ሰራተኛ በመሆን ተቀጥረው እንደሚሰሩ አረጋግጠው ካሉበት ተይዘው እንዲመጡ አደረጉ፡፡
የሀሰት ሟች አቶ ታከለ በሰጡት የዕምነት ቃል ወንጀሉን አቀነባብረው መፈፀማቸው በሰውና በሰነድ ማስረጃ ተረጋግጦ የባህር ዳና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በ24/05/2010 ዓ/ም በዋለው ችሎት በእድሜ ልክ ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ተወስኗል፡፡
በሀሰት ምስክር ለ7 ዓመታት በማረሚያ ቤት የቆዩት ወይዘሮ ሰቀቀን ቆይቶም ቢሆን የእውነት በር ተከፍቶላቸዋል፡፡
የሀሰት ምሰክሮችም ከወራት በፊት የእስራት ቅጣት መቀጣታቸው ይታወሳል፡፡ ይላል የአማራ ክልል ፍትህ ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ባደረሰን መረጃ፡፡
Share your thoughts on this post