አሜሪካ ከ5 ዓመት በታች የሆኑ ህፃናትን ከስደተኛ ወላጆቻቸው ጋር እንደገና ልታገናኝ መሆኑን ባለስልጣናት ገልጸዋል።
ህፃናቱ እንደገና ከወላጆቻቸው ጋር እንደሚገናኙ የትራምፕ አስተዳደር ባለስልጣናት ሮቡ በሰጠው መግለጫ ማረጋገጡም ነው በዘገባው የተገለጸው።
በአሜሪካና ሜክሲኮ ወሰን አካባቢ ህጋዊ ሰነድ ሳይኖራቸው በህገ ወጥ መንገድ ሲገቡ ከቤተሰቦቻቸው የተነጠሉ እድሚያቸው ከ5 ዓመት በታች የሆኑ ህጻናት በሙሉ ከቤተሰቦቻቸው እንዲቀላቀሉ የአሜሪካ የፌደራል ዳኛ ማዘዛቸውም ነው የተገለጸው።
በዚህም በአሜሪካ ህጋዊ ሰነድ ከሌላቻው ስደተኞች የተነጠሉ እድሜቻው ከ5 ዓመት በታች የሆኑ ህጻናት በሙሉ ዛሬ ከቤተሰቦቻቸው እንደሚገናኙ ነው ዘገባው የሚያስረዳው።
ምንጭ፦ reuters.com
የተተረጎመው፦ በእንቻለው ታደሰ
Share your thoughts on this post