ከ1 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ተመለሱ

የሳዑዲ ዓረቢያ መንግስት ምህረት ያደረገላቸው 1 ሺህ 85 ኢትዮጵያውያን ወደ ሃገራቸው ተመልሰዋል።

ወደ ሃገር ቤት የተመለሱት ዜጎች የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ፥ ለሳዑዲ ዓረቢያ ንጉስ በሃገሪቱ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እስረኞች እንዲፈቱ በጠየቁት መሰረት ምህረት የተደረገላቸው ናቸው።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርም ጊዜያዊ አስተባባሪ ኮሚቴ በማቋቋም እና ከተለያዩ የመንግስት አካላት ጋር በመተባበር አቀባበል አድርጎላቸዋል።

ከዚህ ባለፈም አስፈላጊውን አቅርቦት በማዘጋጀትና የሚያርፉበትን ቦታ በማዘጋጀት ድጋፍ ማድረጉን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ከአለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ጋር በመተባበርም ዜጎች ወደ ቤተሰቦቻቸው እንዲቀላቀሉ የትራንስፖርት ድጋፍ ተደርጎላቸው ተሸኝተዋል።

ባለፈው ቅዳሜ ምህረት የተደረገላቸው 690 ኢትዮጵያውያን ወደ ሃገራቸው መመለሳቸው ይታወሳል።

ኤፍ ቢ ሲ

Share your thoughts on this post

Advertisements
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram