ከአንድ ሚሊየን ዶላር በላይ በህገ ወጥ መልኩ ከሃገር ሊወጣ ሲል ተያዘ

በፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ የክልሎች የወንጀል ምርመራ ማስተባበሪያ ምክትል ዳይሬክተር አቶ ፍቃዱ አመንቴ እንዳሉት 591453 የአሜሪካ ዶላር እና 7000 ዩሮ በከባድ ጭነት መኪና እስፒከር ውስጥ ተደብቆ በጅቡቲ በኩል ሊወጣ ሲል አዋሽ ብሄራዊ ፓርክ አካባቢ በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡

በህገ ወጥ የገንዘብ ዝውውሩ ተሳታፊ የሆነው አሽከርካሪ ለተጨማሪ ምርመራ ከነመኪናው በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡

በተመሳሳይም በአዳማ ኬላ ወለንጪቲ መውጫ ላይ 495390 ዶላር በሎቤድ መኪና ተደብቆ ሊወጣ ሲል በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡

በዚህ ህገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር ተሳታፊ በመሆን የተጠረጠሩት አሽከርካሪውና ረዳቱ በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

Share your thoughts on this post

Advertisements
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram