ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኮማንድ ፖስት ሴክሪተሪያት ጽ/ቤት የተላከ ዜና ቀን 12/07/2010 ዓ/ም
ቀን 12/07/2010 ዓ/ም
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኮማንድ ፖስት ሴክሪተሪያት ጽ/ቤት ዜና

በኦነግ የተሳሳተ ወሬ ከሞያሌ እና አከባቢዉ ወደ ኬንያ ተፈናቅለዉ የነበሩ ዜጎች አብዛኛዎቹ ወደ ቀያቸዉ መመለሳቸዉ ተገለፀ ፡፡ ቀሪዎችንም ለመመለስ ጥረቱ ቀጥሏል፡፡
በአሁኑ ወቅት በመላ ሀገሪቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታውጆ ተግባራዊ በመደረግ ላይ ነው፡፡ በዚህም መሰረት ሰላም በመስፈኑ በሁሉም የሃገራችን አቅጣጫዎች ህዝቡ ተረጋግቶ የዕለት ተዕለት ተግባሩን በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡
ይሁን እንጂ የሃገራችንን ሰላምና የህዝቦችን ደህንነት የማይፈልጉ የተለያዩ ሃይሎች የተገኘውን ሰላም ለማደናቀፍ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ናቸው፡፡ ከነዚህፀረ-ህዝብና ፀረ-ሰላም ሃይሎች ውስጥ አንዱ የሆነው አሸባሪዉ ኦነግ የኢትዮጵያን በጎ የማይመኙ ሃይሎችን ተልእኮ ለመፈፀምና ኢትዮጵያን የማተራመስ የቆየ አላማውን ለማሳካት በማሰብ በቅርቡ በሞያሌና አካባቢው ጥቃት እሰነዝራለሁ እያለ በህዝብ ላይ መሰረተ ቢስና የተሳሳተ ወሬ በመንዛት ህዝቡ እንዲፈናቀል አድርጓል፡፡ በዚህም ምክንያት ከ7 ሺ እስከ 8 ሺ የሚገመቱ ሰላማዊ ዜጎች ወደ ኬንያ እንደተፈናቀሉ ቀደም ሲል ተገልፆ ነበር፡፡
ሆኖም የሃገር ሽማግሌዎች፣ አባገዳዎችና በአካባቢው የሚገኘው ኮማንድ ፖስት ባካሄዱት የጋራ ጥረትና የህዝቡን ፍላጎት
ታክሎበት አብዛኛዎቹን ተፈናቅለው የነበሩ ዜጎች ወደ ቀያቸው መመለስ ተችሏል፡፡ የተቀሩትን በመቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎቻችንንም እንዲመለሱ ለማድረግ ተከታታይ ስራ በመሰራት ላይ ነው፡፡
በአሁኑ ወቅት የሞያሌ ከተማና አካባቢው የተረጋጋ ህዝቡም ሰላማዊ የሆነ የዕለት ተዕለት ተግባሩን በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡
በአሁኑ ወቅት የሞያሌ ከተማና አካባቢው የተረጋጋ ህዝቡም ሰላማዊ የሆነ የዕለት ተዕለት ተግባሩን በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡
ይሁን እንጂ የራሳቸው የሆነ ፀረ-ህዝብ አጀንዳ ያላቸው አንዳንድ ግብረ ሰናይ ነን የሚሉ ድርጅቶችና የሚዲያ ተቋማት መሰረተ ቢስና ከእውነት የራቀ ወሬ በማሰራጨት ላይ ይገኛሉ፡፡
በመሆኑም እነዚህ አካላት ከዚህ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ኮማንድ ፖስቱ አስገንዝቦ ከድርጊቸው የማይታቀቡ ከሆነ ግን አስፈላጊ የሆነው ህጋዊ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን አስታዉቋል።
Share your thoughts on this post