fbpx

ከአርቲስት ወይንሸት ጋር ተያይዞ በETV የቀረበው ፕሮግራም ከእውነት የራቀ መሆኑን አርቲስት ዮሴፍ ገብሬ እና የቦርዱ አባላት አስታወቁ

ከአርቲስት ወይንሸት ጋር ተያይዞ በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን የቀረበው ፕሮግራም ከእውነት የራቀ መሆኑን አርቲስት ዮሴፍ ገብሬ አስታወቀ፡፡ አርቲስቷ ኮንዶሚኒየም ቤት ደርሷት እንደነበረ ያስታወሰው አርቲስቱ በገና የዘመድ ጥየቃ ፕሮግራሙ ሲጎበኛትም የቤት እቃ ማሟያ የሚሆን ገንዘብ ከለጋሽ ድርጅቶች አሰባስቦ ሊሰጣት ቃል ገብቶ እንደነበረ ተናግሯል፡፡

ይህን ጉዳይ በቋሚነት የሚከታተለው ኮሚቴ በስራ ጫና ምክንያት ገንዘቡን በወቅቱ ለአርቲስቷ ማድረስ ሳይችል መቅረቱን የሚያምነው ድምጻዊ ዬሴፍ ይህን አጋጣሚ ተጠቅመው የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ጋዜጠኞች የእርሱንና የቴሌቭዥን ጣቢያውን ስም ለማጉደፍ መድከማቸውን ነው የሚናገረው፡፡

ፕሮግራሙን የሰሩት የኢቲቪ ጋዜኞች ከዚህ ቀደም በኛ የቴሌቭዥን ጣቢያ በጋዜጠኝነት ሲያገለግሉ የነበሩና በነበረባቸው የሞያ ስነ ምግባር ጉድለት ሳቢያ ከድርጅቱ እንዲባረሩ የተደረጉ ናቸው ብሏል – የጄቲቪ ኢትዮጵያ የቴሌቭዥን ጣቢያ ባለቤት አቶ ዮሴፍ ገብሬ፡፡

ጆሲን ጨምሮ ሌሎች የጄቲቪ አመራሮች የኢቢሲ ጋዜጠኞች ፕሮግራማቸው ሙሉ ሁኖ መቅረብ እንዲችል እኛንም ሊያናግሩን ይገባ ነበር ሲሉ ቅሬታቸውን ገልጸዋል፡፡ ፕሮግራሙ የድርጅቱንና የእርሱን ስም ለማጥፋት የወጠነ እንደሆነም በግልጽ አስቀምጧል፡፡

በሲውዘርላንድ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ተወካይ የሆነችው ወ/ሮ እስከዳር ተክለ ጊዮርጊስ የተወራውን አይነት ያልተገባ ምግባር ድምጻዊ ዮሴፍ እንዳልፈጸመ አስተባብላ የኢትዮ ዙሪክ የስፖርት ክለብ የለገሰው ገንዘብ አርቲስቷ እጅ አለመድረሱን አስቀድመንም እናውቅ ነበር ብላለች፡፡ አቶ ጆሴፍ በተለያየ ምክንያት ገንዘቡ ለአርቲስቷ እስካሁን እንዳልደረሰ ያሳውቀን ነበር ያለችው ተወካይዋ ኢቢሲ ለምን የስም ማጥፋት ስራ በአርቲስቱና በቴሌቭዥን ጣቢያው ላይ ለመፈጸም እንደወደደ አልገባንም ብላለች፡፡

ምን አዲስ ፕሮግራም ይህን ጉዳይ አስመልክቶ ያዘጋጀውን መሰነዶ እንድትመለከቱት እንጋብዛለን፡፡ መልካም ቆይታ!

Via news.et

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram