fbpx

ከአልኮል ጋር ተያይዞ በሚከሰት የጉበት በሽታ ህይወታቸውን የሚያጡ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ መጠን እየጨመረ ነው ተባላ

ከአልኮል ጋር ተያይዞ  በሚከሰት የኪርሆሲስና የጉበት በሽታ ምክንያት ህይወታቸውን የሚያጡ ሰዎች በከፍተኛ ቁጥር እየጨመረ ነው ተባለ።

በተለይ ከፈረንጆቹ 1999 እስከ 2016 ባሉት ጊዜያት ከኪርሆሲስና ጉበት ጋር በተያያዘ ህይወታቸውን ያጡት አብዛኞቹ በወጣትነትና ጎልማሳነት እድሜ ክልል የሚገኙ ሰዎች እንደሆኑ ተነግሯል።

በጉበት ላይ የሚደርስ ከፍተኛ የሆነ ጉዳት በ65 በመቶ ከፍ እንዳለና ጉዳቱም ከአልኮል ጋር ተያይዞ በሚከሰት ችግር ምክንያት እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን፥ እድሜያቸው ከ25 እስከ 34 የሚገኙ ሰዎች በከፍተኛ ሁኔታ ተጠቂ ናቸው ተብሏል።

የዘርፉ የህክምና ባለሙያዎች እንዳስታወቁት በአሁን ወቅት በጉበታቸው ላይ በከፍተኛ መጠን ጉዳት እየደረሰባቸው የሚገኙት አልኮል በብዛት የሚጠቀሙት ወጣቶች እንደሆኑ ተገልጿል።

ከዚህ ባለፈ በኪርሆሲስ በሽታ ለተጠቁ ሰዎች ለሚደረግ ህክምና በርካታ ቢሊየን ዶላር ወጪ እንደሚደረግ ተነግሯል።

በአልኮል ምክንያት በሚከሰት ሞት  የበርካቶች ህይወት እንዲቃወስ፣ ቤተሰብ እንዲበተን እና አምራች ሀይል የሆነው የወጣት ሃይል በኢኮኖሚው ላይ ውጤታማ እንዳይሆኑ አድርጎል።

ይፋ የተደረገው ጥናት እንዳመለከተው እድሜያቸው ከ25 እስከ 34 በሚገኙ ሰዎች ላይ ከጉበት ጋር ተያይዞ በሚከሰተው ኪርሆሲስ በሽታ ህይወታቸውን እንደሚያጡ የተገለፀ ሲሆን፥ ይህም በየአመቱ የ10 ነጥበ 5 በመቶ ጭማሪ እያሳየ ነው ተብሏል።

የኪርሆሲስ በሽታ በሄፓታይተስ ቫይረስ፣ በጉበት በሽታ እና ከአልኮል ጋር በሚከሰቱ ችግሮች ምክንያት የሚከሰት መሆኑ ተጠቁሟል።

በጥናቱ የተሳተፉ አካላት ይህ ሁኔታ ሊሻሻል እንደሚችል የጠቆሙ ቢሆንም ሁኔታው ከፍተኛ ስራ የሚጠይቅና አስቸጋሪ እንደሚሆን አስታውቀዋል።

በኪርሆሲስና በሽታ ህይወታቸውን የሚያጡ ሰዎች ቁጥር በፈረንጆቹ 2009 ተከስቶ በነበረው የኢኮኖሚ ቀውስ ከፍ ብሎ እንደነበረ ነው የተነገረው።

ተመራማሪዎቹ የአልኮል ተጠቃሚነት ከፍተኛ መሆንና ስራ አጥነት ተያያዥነት እንዳላቸው የገለፁ ሲሆን፥ተጨማሪ ጥናቶች ግን እንደሚያስፈልጉ ጠቁመዋል።

በኪርሆሲስና ምክንያት ባለፉት ሰባት ዓመታት 460 ሺህ 760 ሰዎች ህይወታቸውን ያጡ ሲሆን፥ በ2016 ብቻ 11 ሺህ 73 ሰዎች በጉበት ካንሰር ህይወታቸውን እንዳጡ ነው የተነገረው።

ምንጭ፦ ሳይስዴይሊ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram