fbpx

እብድ ውሻ በተርጫ ከተማ ነዋሪዎች ላይ ጉዳት አደረሰ

በዳውሮ ዞን ተርጫ ከተማ እብድ ውሻ ባደረሰው ጉዳት የ2 ህፃናት ህይወት ማለፉን ተከትሎ የእንስሳት እርድ ከቆመና ስጋ መብላት ከተከለከለ ሁለት ሳምንታት እንዳለፈው የከተማው አስተዳደር አስታውቋል።

የከተማዋ አስተዳደር ማህበራዊ ዘርፍ ተቋማት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ በላይነህ ጆቡላ በበሽታው የተለከፉ የከተማ ነዋሪዎች በተርጫ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ነው ብለዋል።

በከተማዋ የሁለት ህፃናት ህይወት በበሽታው ምክንያት እንደጠፋም ነው የተገለጸው።

የእርድ አገልግሎት ለጊዜው መቋረጡን የተናገሩት የታርጫ ከተማ ከንቲባ አቶ አንበሴ ኡሩኩ በሽታው ከእብድ ውሻ ወደ እንስሳት፣ ከእንስሳትም ወደ ሰው ሊተላለፍ የሚችል መሆኑ በምርመራ ተረጋግጧል ብለዋል።

በሽታው የከፋ ጉዳት ከማድረሱ በፊት ለመከላከል ግብረሃይል ተቋቁሞ እየሰራ ነው ያሉት ከንቲባው ባለቤት የሌላቸውን ውሾች ለማስወገድ የኬሚካል እጥረት እንዳለ አመላክተዋል።

ባለቤት የሌላቸው ውሾቹን የማስወገድ ስራ እየተሰራ ሲሆን፥ በሽታው በቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ መደበኛው የእርድ አገልግሎት የሚጀምር መሆኑን አስረድተዋል።

የእርድ አገልግሎቱ በመቆሙ በከተማዋ በምግብ አገልግሎት የተሰማሩ ሰዎችን ገቢ የቀነሰው ቢሆነም ከጤና የሚበልጥ ነገር ባለመኖሩ ሁኔታው እስኪስተካከል ድረስ በትግስት እንጠብቃለን ሲሉ አስተያየታቸውን እንደሰጡም ነው የተገለጸው።

ኢ.ዜ.አ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram