fbpx
AMHARIC

እሳቱ አልጠፉም! – የሸካ ጥብቅ ደን የእሳት አደጋ ገጥሞታል

በጌትነት ተመስገን

° በአለም ቅርስነት የተመዘገበ ስፍራ ነው
° ከመቶ ሄክታር በላይ ደን በእሳቱ ሙሉ በሙሉ ወድሟል፡፡
° እሳቱ ከአካባቢው ማህበረሰብ አቅም በላይ ሆኗል፡፡

በአለም የስነ ህይወት ቅርስ በዩኔስኮ የተመዘገበው የሸካ ጥብቅ ደን የእሳት አደጋ ገጥሞታል፡፡ ካለፈው አርብ ጀምሮ በምን ምክንያት እንደተነሳ ባልታወቀ አሳት እየተቃጠለ ይገኛል፡፡

እስከ ዛሬ ድረስ ከአንድ መቶ ሄክታር በላይ በቃጠሎ ጉዳት የደረሠበት ሲሆን ከአካባቢው ማህበረሰብ አቅም በላይ እንደሆነ የዞኑ አስተዳደር ገልፆ የሚመለከታቸው ሁሉ አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲደረግላቸው ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የሸካ ጥብቅ ደን በውስጡ የተለያዩ ከ3 መቶ በላይ የዛፍ ዓይነቶች፣ 50 አጥቢ የዱር እንስሳት፣ 200 የወፍ እና 20 የተሳቢ እንስሳት ዝርያዎች ይገኙበታል፡፡

ከእነዚህ መካከልም ቢያንስ 55 የእፅዋትና 10 የወፍ ዝርያዎች በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙ ናቸው፡፡

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram