fbpx

ኤርትራ ጦሯና ማንቀሳቀስ ጀመረች፡ ኢትዮጵያስ?

ኤርትራ ጦሯና ማንቀሳቀስ ጀመረች ፡ኢትዮጵያስ?| ሬሞንድ ሃይሉ 

ወዲ አፎም ባልተለመደ መልኩ ለፍቅር እጅ እየሰጡ ይመስላል፡፡ የኤርትራ ፕረስ ድርጅት ትናንት በፌስቡክ ገጹ ባቀረበው ዜና እንዳስታወቀው የኤርታራ ጦር የሁለት አስርታት ምሽጉን ተሰናብቶ ከድንበር አከባቢ መንቀሳቀስ ጀምሯል፡፡

የተለያዩ ዓለም አቀፍ የወሬ ምንጮችም ይህን የኤርትራ መንግስት ተግባር አስገራሚና የማይታመን እያሉ እያሞካሹት ይገኛሉ፡፡

ጥቂት የማይባሉ የዜና አውታሮችም ለአስገራሚው የኤርትራ መንግስት ውሳኔ መነሻው ምን ሊሆን ይችላል የሚል ጥያቄ እየሰነዘሩ ነው፡፡

ኳታር ጀምራው የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የጨረሰችው የሁለቱ ሀገር የሰላም ጉዳይ ሪሞትም በአሜሪካ እጅ እንደሚገኝም ብዙዎች ይገልጻሉ፡፡

እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ዕርቁ በማንም ገፊ ምክንያት ይምጣ በማን ትርጉም ያለው አይመስለኝም፡፡ የአሜሪካን ውጭ ጉዳይ ሚንሰትር የአፍሪካ ረዳት ሃላፊ የነበሩት ዶናልድ ያማማቶ ይደከሙበትም የተባበሩት አረብ ኤምሬትሶች ንጉስ ፡ ኢትዮጵያና ኤርትራ ወደ ስላም የሚያደርሳቸውን መንገድ መጥረግ ጀምረዋል፡፡ ዘላቂ ሰለመሆኑ እርግጠኛ መሆን ባይቻል እንኳን በጊዜያዊ ሰላሙ በርካቶች ከቤተሰባቸው ጋር ተገናኝተዋል፡፡

ከጦርነት ኢዚም ወጥተን ሰለሰላም ማውራታችን በራሱ ትልቅ ድል መሆኑ አያከራክርም፡፡ እዚህ ላይ ግን ያሉ ስጋቶችን በተራ የቃላት ጨዋታ ብቻ እንሻገራለን ብሎ ማሰብ የዋህነት ነው፡፡ የመለያየት ግንብ ፍረስ የፍቅር ድልድይ ተገንባ ስላልንም የሚፈጠር ዕርቅ አይኖርም፡፡ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ዕርቅ ዕውን የሚሆነው በመርህ ላይ በተመሰረተ ውይይትና ድንበር ላይ ያለው ህዘብ ካለገደብ ወደ ነበረበት ወንድማማችንት መመለስ ሲችል ነው፡፡

ይህ ምኞት ከዳር እንዳይደርስ ግን ሁለት ስጋቶች ከፊታችን ተደቅነዋል፡፡ የመጀመሪያው የባድመ ጉዳይ አሁንም አዲስ የሙግት ምህዳር መክፈቱ ሲሆን ሁለተኛው በአንጻሩ የመከላክያ ኃይላችን ለዚህ ተግባር ያለው ተነሳሽነት ነው ፡፡

የባደመ ጉዳይ በተደጋጋሚ የተነሳና በርካታ የድንበር ነዋሪዎች በስለፍ ተቃውሟቸውን የገለጹበት በመሆኑ በዚህ ጽሁፍ በድጋሚ ለመዳሰስ አልሞክርም ፡፡

ከከዚህ በመነሳት የኢዮጵያ መከላክያ ኃይል ለዕርቁ ምን ያህል ዝግጁ ነው የሚለውን ብቻ ለመፈተሸ እንሞክር፡፡ የኢትዮጵያ መከላክያ ኃይል ከማንም በላይ በማያውቀው የፖለቲካ ጨዋታ ውስጥ እራሱን መስዕዋት ሲይደርግ ኑሯል፡፡

ከማንም ኢትዮጵያዊ በላይም በሁለቱ ሀገራት ፖለቲከኞች ጸብ የተነሳ እራሱን ሻማ አድርጎ ለሀገር ደጀን መሆኑን አሳይቷል ፡፡ በዚህ የተነሳም ስለዕርቁ ሲነሳ ከማንም በላይ የሚመለከተው አካል መሆኑ አያከራክርም፡፡

በመከላክያ ሰራዊቱ የስልጠና ማንዋሎች ላይ በግልጽ እንደሰፈረው የ.ኢፌ.ዴ.ሪ መከላክያ ኃይል ተነሳ ተዋጋ ሲባል ተነስቶ የሚዋጋ ሳይሆን የሚሞትለትን አላማ በውሉ የተረዳ እንዲሆን ሲሰራ ኑሯል፡፡ እንዲህ ከሆነ የመከላክይ ኃይላችን ኤርትራ ድንበር ላይ ሁለት አስርታትን ሲያሳልፍም ሆነ ከዛ ስፍራ ተነሳ ሲባል ለምን ብሎ መጠየቁ አይቀሬ ነው፡፡

የዘጋርድያኑ ጋዜጠኛ ማርክ አንደርሰን የሰሞኑን ዜናም የመከላክያ ኃይሉ ለምን ብሎ መጠየቁን የሚያሳይ ይመስላል፡፡ አንደርሰን እንደገጸው የኢትዮጵያ መከላክያ ስራዊት በሀምሌ ወር መግቢያ ከድንበር አከባቢ እንዲለቅ በጠቅላይ ሚንሰትር ዐብይ ትዕዛዝ ቢሰጠውም እስካሁን ግን ትዕዛዙን አልፈጸመም፡፡

ከፕሬዘዳንት ኢሳይያስ የኢትዮጵያ ጉብኝት በፊት ታስቦ የነበረው የድንበር አከባቢን ከወታደራዊ እንቅስቃሴ ነጻ የማድረግ ፍላጎት ያልተሳካውም በዚህ ምክንያት ይመስላል፡፡

በርግጥ የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የአልጀርስን ስምምነት ተቀብያለሁ ካለ በኋላ የመከላክያ ስራዊቱ የተደበላለቀ ስሜት እንዳደረበት ሲገለጽ ቆይቷል፡፡

ጉዳዩ በይበልጥ የሚመለከተው የሰሜን ዕዝ አብዛኛው የሰራዊት አባልም የኢህአዴግን ውሳኔ መቃወሙ በወቅቱ የተሰማ እውነታ ነው፡፡ እንዲህ ከሆነ ኤርትራ ጦሯና ማንቀሳቀስ ጀመረች ፡ኢትዮጵያስ ? ብለን መጠያቃችን ዕርግጥ ይሆናል፡፡

መላሹ ግን እንደ ጥያቄው ቀላል አይደለም ፡፡ ህይወቱን፣አካሉንና ዕድሜውን ገብሮ ድንበር ሲጠብቅ ለኖረው ሰራዊት አሁንም አሳማኝ ምክንያት ሊሰጠው ይገባል ፡፡ ይህ ደግሞ ህገ-መንግስታዊ መብቱም ነው፡፡! DireTube

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram