ኢትዮ ቴሌኮም ወደ ኤርትራ ስልክ ለመደወል የሚያስፈልገውን ዝርዝር መረጃ ይፋ አደረገ

ኢትዮ ቴሌኮም ወደ ኤርትራ ወደ መደበኛና የሞባይል ስልክ ለመደወል የሚያስችለውን ዝርዝር መረጃ ይፋ አደረገ።

የኢትዮ ቴሌኮም እንዳስታወቀው ደንበኞች ወደ ኤርትራ የመደበኛና ሞባይል ስልኮች ሲደውሉ ታሪፉ ቫትን ጨምሮ ለአንድ ደቂቃ 10 ብር ከ29 ሳንቲም እንዲሁም ለአጭር የጽሁፍ መልእክት ብር 6.10  ነው።

ኩባንያው እንዳስታወቀው ወደ ኤርትራ መደበኛ ስልክ ለመደወል +291 1 እና ለሞባይል ስልክ ደግሞ +291 7 በማስቀደም የሚደወልለትን ስልክ ቁጥር በማስገባት አገልግሎቱን ማግኘት እንደሚቻል ገልጿል።

በአሁን ወቅት የተቋሙ ደንበኞ ወደ ኤርትራ መደበኛና የሞባይል ስልክ መደወል እንደሚችሉም ነው ያስታወቀው።

ከኤርትራ ጋር የነበረው የስልክ ግንኙነት ከ1990 ዓ.ም ጀምሮ ተቋርጦ እንደቆየ የተገለፀ ሲሆን፥ ከ20 ዓመታት በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በኤርትራ ያደረጉትን ጉብኝት ተከትሎ አገልግሎቱ በድጋሚ ተጀምሯል።

Share your thoughts on this post

%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram