fbpx

HT

ሐበሻ ታይምስ ሚዲያ

AMHARIC

ኢትዮጵያ የፀጥታው ምክር ቤት በኤርትራ ላይ የጣለውን ማዕቀብ እንዲያነሳ ይፋዊ ጥያቄ አቀረበች

ኢትዮጵያ የመንግስታቱ ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት በኤርትራ ላይ የጣለውን ማዕቀብ እንዲያነሳ ይፋዊ ጥያቄ አቀረበች።

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በኤርትራ ያደረጉትን ይፋዊ ጉብኝት አጠናቀው አዲስ አበባ ገብተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አዲስ አበባ ከተመለሱ በኋላ ከመንግስታቱ ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ጋር ተወያይተዋል።

በዚህ ወቅትም ተመድ በኤርትራ የጣለውን ማዕቀብ እንዲያነሳ ለዋና ፀሃፊው ይፋዊ ጥያቄያቸውን አቅርበዋል።

ጥያቄው የቀረበላቸው የመንግስታቱ ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በበኩላቸው፥ ኤርትራ ላይ የተጣለው ማዕቀብ ከዚህ በኋላ ብዙ ጊዜ ተግባር ላይ እንደማይቆይ ተናግረዋል።

ዋና ፀሃፊው ኢትዮጵያና ኤርትራ መደበኛ ግንኙነታቸውን ለመጀመር መስማታቸውን ተከትሎ፥ ምክር ቤቱ በኤርትራ ላይ የጣለው ማዕቀብ ከዚህ በኋላ ተግባር ላይ የሚቆይበት ምክንያት የለም ብለዋል።

ከዚህ ባለፈም ዋና ፀሃፊው ሁለቱ ሃገራት ከድንበር ጋር በተያያዘ የደረሱት የድንበር ማካለል ጉዳይ እንዲሳካም ተመድ ሁኔታዎችን ለማመቻቸት ዝግጁ መሆኑንም ገልጸዋል።

eth_eu.jpg

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በኤርትራ በነበራቸው ቆይታ ከፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር የተለያዩ ስምምነቶችን ተፈራርመዋል።

በስምምነታቸው ወቅትም በኤርትራ ላይ የተጣሉ ማዕቀቦች እንዲነሱና በአለም አቀፍ የፖለቲካ መድረክ እየደረሰባት ያለው መገለል እንዲያበቃ፥ ኢትዮጵያ ትሰራለች ማለታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ መግለጻቸው ይታወሳል።

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram