fbpx

HT

ሐበሻ ታይምስ ሚዲያ

AMHARIC

ኢትዮጵያ በታንዛኒያና ዘ ሄግ ኤምባሲዎቿን ልትከፍት ነው

ኢትዮጵያ በአለም አቀፍ መድረኮች የዲፕሎማሲ ሚናዋን ከፍ ለማድረግ ሁለት አዲስ ኤምባሲዎችን ልትከፍት መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ ለህዘብ ተወካዮች ምክር ቤት የዘጠኝ ወር የስራ አፈጻጸም ሪፖርቱን ሲያቀርበ ነው ይህንን ያሳወቀው።

የወጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ እንዳሉት፥ የእስያ አህጉር የኢትዮጰያ የገበያ መዳረሻና የኢንቨሰትመንት ቀዳሚ ምንጭ በመሆኑ ባለፉት ዘጠኝ ወራት በኢንዶኔዢያ ኢምባሲ ተከፍቶ ስራ ጀምሯል።

በቀጣይም ሁለት አዳዲስ ኢምባሲዎች በአውሮፓ ኔዘርላንድስ ዘ ሄግ ከተማ እና በአፍሪካ ደግሞ ታንዛንያ ዳሬሰላም ከተማ ለመክፈት ዝግጅቶች ተጠናቀዋል ነው ያሉት።

ስምንት የክብር ቆንስላዎችም በፓሪስ፣ አዘርባጃን፣ ቶጎ፣ ኢኮቶሪያል ጊኒ፤ እንዲሁም በሲንጋፖር፣ በደቡብ ኮርያ እና በካልጋሪ እንደተሾሙም አብራርተዋል።

ሚኒስቴሩ ቀጥተኛ የውጭ ኢንቨስትመንትን ለመሳብም ከእስያ፣ አውሮፓ፣ መካከለኛው ምስራቅ እና ሌሎች ክፍለ አለማት የመጡ 64 ትልልቅ ኩባንያዎች ሀገሪቱን እንዲጎበኙ ማድረጉን ነው ያነሱት።

22 ኩባንያዎችም በቆዳና ቆዳ ዉጤቶች፣ በጨርቃ ጨርቅና አልባሳት፣ በግንባታና ሌሎች ዘርፎች ወደ ስራ እንዲገቡ መደረጉንም ተናግረዋል።

በቤተልሄም ጥጋቡ – ኤፍ.ቢ.ሲ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram