fbpx

HT

ሐበሻ ታይምስ ሚዲያ

AMHARIC

ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን አሳፍራ ወደ የመን ስታመራ የነበረች ጀልባ ሰጥማ 46 ኢትዮጵያውያን ሞቱ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 30፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮጵያውያን ስደተኖችን አሳፍራ ወደ የመን ስታመራ የነበረች ጀልባ መስጠሟን የተመድ ባለስልጣናት ገልጸዋል።

ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት እንዳስታወቀው ጀልባዋ ረቡዕ ጧት በኤደን ባህረ ሰላጤ አካባቢ የሰጠመች ሲሆን፥ ጀልባዋ ላይ ከነበሩት ውስጥ የ46 ተሳፋሪዎች ህይወት ማለፉ ነው የተገለጸው።

በአደጋው ህይወታቸውን ያጡትም 37 ወንዶች እና  9 ሴቶች ሲሆኑ፥16 ሰዎች ደግሞ እስካሁን የገቡበት አልታወቀም።

ከቦሳሶ ወደብ የተነሳችው ጀልባዋ 100 ያህል ስደተኞችን አሳፍራ ወደ የመን ስታመራ የነበር መሆኑን የነፍስ አድን ስራ ላይ የተሰማሩ ሰራተኞች ገልጸዋል።

ተጨናንቀው የተጫኑት እነዚህ ስደተኞቹ የአደጋ ጊዜ መንሳፈፊያ ጃኬትም ለጉዞው ያልተዘጋጀላቸው መሆኑ ተመላክቷል።

በዚህ ህይወትን አደጋ ላይ በሚጥል አስቸጋሪ ጉዞ በየወሩ 7 ሺህ ያህል ስደተኞች የሚጓዙ ሲሆን፥ ባለፈው ዓመት ብቻ 100 ሺህ ያህል ስደተኞች ከአደጋ መታደጉን ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ባለ ስልጣን የሆኑት ሞሀመድ አብዲከር ገልጸዋል።

አካባቢው ወደ አረብና አውሮፓ ሀጋራት መተላለፊያ መስምር በመሆኑ ስደተኞች የሚመርጡትና ከላፉት አስርት አመታት ጀምሮ በዚህ በኩል እንደሚያልፉም ነው ዘገባው የሚየመላክተው።

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram