fbpx

ኢትዮጵያና ኬንያ ሞያሌ የምስራቅ አፍሪካ የቢዝነስ ማዕከል ለማቋቋምና በኬንያ የታሰሩ ዜጎችን እንዲፈቱ ተስማሙ

ኢትዮጵያና ኬንያ ሞያሌ የምስራቅ አፍሪካ የቢዝነስ ማዕከል ለማቋቋምና በኬንያ የታሰሩ ዜጎችን እንዲፈቱ ተስማሙ

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ እና የኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ዛሬ ናይሮቢ ቤተ መንግስት ተወያይተዋል።

ሁለቱ መሪዎች የኢትዮጵያ እና ኬንያ ሞያሌ ከተሞችን የምስራቅ አፍሪካ የቢዝነስ እና ንግድ ማዕከል እንድትሆን በጋራ ለማልማት ተስማምተዋል። መሪዎቹ የሁለቱ ሀገሮች አንጋፋ መሪዎች የሆኑት ቀዳማዊ ኃይለስላሴ እና ጆሞ ኬንያታ ያስቀመጧቸው የልማት፣ ትብብርና የህብረት ራዕይ ለማሳካትና ግንኙነቱን ከፍ ወዳለ ደረጃ ለማድረስ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።

በኬንያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ክብራቸው ተጠብቆ እንዲኖሩ በተለያዩ ምክንያቶች እስር ቤት ያሉ ወገኖቻችንም እንዲለቀቁ ዶ/ር አብየ ጠይቀው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ስምምነታቸውን ገልጸዋል።

ሁቱ መሪዎች የኢትዮጵያ እና ኬንያ ሞያሌን በጋራ ለማልማት የምስራቅ አፍሪካ የቢዝነስና ንግድ ማዕከል እንድትሆን በጋራ እንሰራለን ብለዋል።

የኢትዮጵያ የታሪክና የተፈጥሮ ሀብትን እንዲሁም የኬንያ የታሪክና የተፈጥሮ ሀብትን መሰረት ያደረገ የቱሪስት መዳረሻነትን በቱሪዝም መስክ ለመተባበርም ስምምነት ደርሰዋል።

በአካባቢ ጉዳዮች፣ በአለምአቀፍ መድረኮች አሸባሪነትን በጋራ ለመዋጋትና በዲፕሎማሲው መስክ አቋሞችን ለማቀናጀት በሶማሊያ እና ደቡብ ሱዳን ሰላም እንዲመጣ በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል።

የኢትዮጵያና ኬንያ አየር መንገዶች በጋራ የሚሰሩበትን ሁኔታ ለማመቻቸት ስምምነት ላይ ደርሰዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

ቃል አቀባይ ጽ/ቤት

ሚያዝያ 29 ቀን 2010 ዓ.ም.

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram