fbpx

ኢቢሲ ተቀይሯል ብቻ ሳይሆን ቀይሮናል

የተደመረው የአሁኑ የኢቢሲ መሪ የቀድሞው የአማራ ብዙሃን ሃላፊ አቶ ስዩም ሊደነቁ የሚገባቸው ሰው ናቸው፡፡

ኢቢሲ ሃምሳ ዓመት አሽቃብጦ በመቶ ቀን የእኛ ሚዲያ ለመሆን በቃ፡፡

ከዚህ ቀደም የስቆቃችን ምልክቶች፣ የአድርባይነት መገለጫ፣ የሀሰት መለያዎች የነበሩ ባለሙያዎች ቢያንስ በአግባቡ እስኪታረሙ ከፊት ባይመጡስ?
***** ስናፍቅሽ አዲስ በድሬቲዩብ

ኢቢሲ ተቀይሯል ብቻ ሳይሆን የሚባለው ቀይሮናል፡፡ አምስት አስርት ዓመት የማናምነው ብሔራዊ ቴሌቨዥናችን በመቶ ቀናት ውስጥ ልባችን መግባት ጀምሯል፡፡ እውነት የሚናገር ጣቢያ ሆኗል፡፡ ከዚህ ቀደም የምናየቸው የእውነት ልሳን የሚባሉትን የግል ሚዲያዎች መቅደም ጀምሯል፡፡

ይሄ ለውጥ ዝም ብሎ አልመጣም፡፡ ጉምቱ ባለስልጣናት ኢቢሲን ለመቀየር ተመድበው ገብተው ተቀይረው ወጥተዋል፡፡ ጤናማው ሰውዬ ከወራት የኢቢሲ አመራርነቱ በኋላ ስኳር በሽታውን ይዞ ይወጣል፡፡ ተረኛው ይገባል፡፡ ኢቢሲ ትንሽ ተስፋ ሰጪ ምልክቶች ታይተውበት የነበረው በወይዘሮ ሰሎሜ የአመራርነት ዘመን ነበር፡፡

አማራ ብዙሃን እንዲህ ተቀባይ ይሆን ዘንድ የብአዴን ሹምምንት በተለይም አቶ ገዱ እና አቶ ንጉሡ ያበረከቱት አስተዋጽኦ ላቅ ያለ ቢሆንም፡፡ እንደ አቶ ስዩም ያሉ የስራ ሃላፊዎች ሚና የአንበሳውን ድርሻ ይይዛል፡፡

አቶ ስዩም ኢቢሲ ከመጣ በኋላ በእርግጥ ወዲያው ኢቢሲ እንደ አማራ ቴሌቨዥን መሆን አልቻለም፡፡ ይሄ የሚያሳየው የሀገር መሪውም ሚና ከፍ ያለ መሆኑን ነው፤ ዶክተር አብይ ቤተ መንግስት ሲገቡ የአቶ ስዩም አቅም መታየት ጀመረ፡፡

ኢቢሲ ተወዳጁ ብቻ ሳይሆን ሃምሳ አመት የገነባውን ስም መልሶ ተጎናጸፈ፡፡ ስሙን እንጂ አሰራሩን መቀየር ያልፈለጉ ሰዎች ያበላሹት ቤት በጤነኛ አመራር ተቀየረ፡፡

አቶ ስዩም ሊደነቁ የሚገባቸው የሚዲያ መሪ ናቸው፡፡ ሀገር መሪ ካላት ሚዲያ የሚመሩ ብቁ ባለሙያዎች እንዳሉን ማሳያ ናቸው፡፡ እናም ክብር ይገባቸዋል፡፡ ሃምሳ አመት አሽቃብጦ፣ ሃምሳ አመት ዋሽቶ፣ ሃምሳ አመት አሸማቆ በመቶ ቀን ከተቀየረው ቴሌቨዥን ጣቢያ ጋር ስማቸው የሚነሳ ታላቅ ሰው ናቸው፡፡

በእርግጥ ኢቢሲ አሁንም ብዙ መስራት ይጠበቅበታል፡፡ ከዚህ ቀደም የስቆቃችን ምልክቶች፣ የአድርባይነት መገለጫ፣ የሀሰት መለያዎች የነበሩ ባለሙያዎች ቢያንስ በአግባቡ እስኪታረሙ ከፊት ባይመጡስ? አሁንስ ቢሆን በለመዱት የመገለባበጥ ባህል እየጮኹ ቢሆን?

ሰው በእነኚህ ባለሙያዎች የሚነገረውን ነገር ሁሉ በትናንቱ ስሜት ከተረዳው ተግባቦቱ ዜሮ መሆኑ አይቀርም፡፡ የሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ኢስላማዊ መንግስት ሊመሰርቱ የነበሩ ናቸው ያለ ሰው አሁን እንዴት ስለ እነኚህ ወገኖች ሰናይ ነገር ሲያወራ እንቀበለዋለን፡፡ የሚፈትነን ሰዋዊ ባህሪያችን ነው፡፡ እንዲህ ያለው ስሜት እስኪበርድ እነኚህ ጋዜጠኞች እንደትናንትናው ከፊት እንሁን ባይሉና ከኋላ እየሰሩ ቆይተው መንፈሱ ሲበረታ ብቅ ቢሉ መልካም ነው፡፡ DireTube

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram