fbpx
AMHARIC

ኡበር አሽከርካሪ አልባ መኪናው የአንድ ሰው ህይወት ማጥፋቱን ተከትሎ የሙከራ ፕሮግራሙን አቋረጠ

በዩናይትድ ስቴስ አሪዞና ግዛት የኡበር አሽከርካሪ አልባ መኪና አንድ ሰው በመግደሉ ምክንያት የሙከራ ፕሮግራሙን ማቋረጡን አስታወቀ።

የ49 ዓመቷ ኢሌን ኸዝበግ የተገጩት መንገድ በመሻገር ላይ ሳሉ መሆኑ ተገልጿል።

የኡበር ስራ አሰኪያጅ ዳራ ኮስሮሻሂ “እጅግ አሳዛኝ ዜና” ነው ብለዋል።

ፖሊስ አደጋው ከደረሰ በኋላ ተጎጂዋን አቅራቢያ ወደሚገኝ ሆስፒታል ቢወስዳቸውም መትረፍ እንዳልቻሉ ጠቅሷል።

በተጨማሪም ኸዝበግ በወቅቱ ለእግረኞች በተቀመጠው መሻገሪያ ላይ እንዳልተሻገሩ ነው ፖሊስ የገለፀው።

የከተማው ከንቲባ ማርክ ሚሼል የቴክኖሎጂውን መምጣት እንደሚደግፉ የተናገሩ ሲሆን፥ ኃላፊነት እንደሚሰማው ተቋም አደጋውን ተከትሎ ኡበር የጀመረውን የሙከራ ፕሮግራም በማቋረጡም አመስግነዋል።

የዩናይትድ ስቴስ የፍጥነት መንገድ አስተዳዳሪና የብሄራዊ ትራንስፖርት ደህንነት ቦርድ ጉዳዩን የሚያጣራ ቡድን ወደ አሪዞና እንደሚልኩ አሳውቀዋል።

ኡበር በራሳቸው የሚሽከረከሩ መኪኖችን የሙከራ አገልግሎት የጀመረው በ2016 መሆኑ ይታወሳል።

አገልግሎቱን ከጀመረባቸው አምስት ከተሞች መሐል አሪዞና ቴምፔ አንዷ ናት።

 

 

 

 

 

ምንጭ፦ ቢቢሲ
ተተርጉሞ የተጫነው፦ በአብረሃም ፈቀደ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram