አፕል ወላጆች የህጻናት ልጆችን የስልክ አጠቃቀም መቆጣጠር የሚያስችል ገጽ ይፋ አድርጓል
አፕል ወላጆች የልጆቻቸውን የስማርት ስልኮችን አጠቃቀም መቆጣጠር እና መገደብ የሚያስችል ገጽ ለወላጆች አቅርቧል፡፡
በባለፈው ጥር ወር ሁለት ታዋቂ ባለሃብተች የአፕል የስማርት ስልኮችን ለህጻናቶች የተመቸ አጠቃቀም እንዲኖር የማድረግ ስራዎችን አልሰራም በሚል መንቀፋቸውን እና ተቋሙ ወላጆች የልጆቻቸውን አጠቃቀም መከታተል የሚያስችሉ አማራጮችን እንዲያቀርብ ጥሪ አቅርበው ነበር፡፡ ህጻናት ለአይፎን ያላቸው ፍቅር ከፍ ያለ መሆኑ ደግሞ በአፕል ተቋም ላይ ችግሮችን እየፈጠረ መሆኑ ይነገራል፡፡
አፕልም ይህን ወቀሳ ተከትሎ ወላጆች ህጻናት ልጆቻቸው መች እና እንዴት የአይፎን የስማርት ስልኮች እንደተጠቀሙ የሚያሳይ ምቹ ሁኔታን የመፈጠረ ገጽ አቅርቧል፡፡
አዲሱ የወላጆች ገጽም apple.com/families — በሚለው ወላጆች ገብተው ማግኘት እንደሚችሉ የገለጸው ተቋሙ በገጹ አማካኝነት ወላጆች የህጻናት ልጆቻቸውን አድራሻ፣ አጠቃቀማቸውን የመቆጣጠር እና መወሰን እንዲሁም ህጻናቱ በስልኮቻቸው የሚጠቀሙዋቸውን ይዘቶች የማጥለል ተግባራትን መከወን ያስችላል ተብሏል፡፡
የኮመን ሴንስ ተቋም ያወጣው የጥናት ውጤት 98 ከመቶ ህጻናቱ በቤት ውስጥ የሚጠቀሙዋቸው የሞባይል ስልኮችን ሲሆኑ በቀን በአማካኝ 48 ደቂቃዎችን በስልኮቻቸው አንደሚያሳልፉ ጠቅሷል፡፡ ከእነዚህ ታዳጊዎች መካከልም 42 በመቶዎቹ የራሳቸው ስልክ ያላቸው እንደሆነ ጥናቱ አመልክቷል፡፡
ምንጭ:- ሲኤንኤን