fbpx

አፈጉባዔ ሙፈሪሃት ካሚልና የምክር ቤቱ አባላት በመስቀል አደባባይ የቦንብ ፍንዳታ ጉዳት የደረሰባቸውን ዜጎች ጎበኙ

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባዔ ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚልና የምክር ቤቱ አባላት በመስቀል አደባባይ የቦንብ ፍንዳታ ጉዳት የደረሰባቸውን ዜጎች ጎበኙ።

አፈጉባዔ ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚልና የምክር ቤቱ አባላት በቅዱስ ጴጥሮስና በየካቲት 12 ሆስፒታሎች በመገኘት ጉዳት የደረሰባቸው ዜጎችን የጎበኙ ሲሆን፥ በደረሰው ጉዳት ከልብ ማዘናቸውንና በጉዳቱ ህይወታቸውን ላጡ ዜጎች ቤተሰቦች መጽናናትን ተመኝተዋል።

ከአማራ ክልል ርዕሰ መስረዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸውና የካቢኔ አባላት ጋር በመሆን ነው በመስቀል አደባባዩ የቦምብ ፍንዳታ ጎዳት የደረሰባቸውን ዜጎች በሚኒልክ ሆስፒታል በትናትናው ዕለት በመገኘት ጎብኝተዋል

የኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ አመራሮች በመስቀል አደባባይ የቦንብ ፍንዳታ አደጋ ጉዳት ደርሶባቸው በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ተገኝተው የህክምና ክትትል ላይ ያሉትን ተጎጂዎች መጎብኘታቸው ይታወሳል።

የኦሮሚያ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ወይዘሮ ጠይባ ሃሰን እና የኦህዴድ ጽህፈት ቤት ሃላፊ ወይዘሮ አዳነች ሃቢቤ ጨምሮ ከፍተኛ የክልሉ ባለስልጣናት በቦምብ ፍንዳታው ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎችም ደም ለግሰዋል።

በተጨማሪም የሀይማኖት አባቶች እና የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችም በመስቀል አደባባይ የቦንብ ፍንዳታ አደጋ ጉዳት የደረሰባቸውን ዜጎች ተጎጂዎችን ጎብኝተዋል።

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram