fbpx

አፄ ቴዎድሮስ በመቅደላ ራሳቸውን በክብር ያጠፉበት ሽጉጥ በአንድ የፈጠራ ባለቤት ተሰርቶ ሙዝየም ገባ

በ1860 ዓ/ም ዳግማዊ ቴዎድሮስ ራሳቸውን በክብር ያጠፉበት ሽጉጥ ከታሪክ ሁነቶች ጋር በማገናዘብ ተሰርቶ ትናንትና ወደ ሙዚየም ገብቷል፡፡

የፈጠራው ባለቤት ወጣት ሃይሉ ሽባባው እንደሚለው ሽጉጡ ከዘመን እና ከታሪክ ጋር የተዋኸደ ነው፡፡

ሽጉጡም ከፁሁፍ ሀሳቦች የተቀዳ ሲሆን 20 ሜትር ድረስ መተኮስ ይችላል፡፡
የጎንደር ከተማ አስተዳደር የባህል እሴቶች አስተባባሪ የሆኑት አቶ ዮናስ ይትባረክ ሽጉጡ በታሪክ አጥኝዎች ስምምነት የተሰራ እንደሆነ አረጋግጠዋል፡፡

የሽጉጡ ፈጠራ ባለቤት ወጣት ሃይሉ ሽባባው ሽጉጡ መተኮስ ይችላል፡፡ የተሰራውም ከአካባቢ በሚገኙ ቀላል ቁሳቁሶች ነው፡፡

ወጣት ሃይሉ ሽባባው በ 2009 ዓ/ም ባለአራት እግር ተሽከርካሪ ባጃጅ ሰርቷል፡፡
ባጃጇ ዛሬም አገልግሎት እየሰጠች ትገኛለች፡፡ ወጣት ሃይሉ ራሱ በሰራት ባጃጅ መገልገል እና አገልግሎት መስጠት ከጀመረ ዓመት ሞልቶታል፡፡

የአፄ ቴዎድሮስ ሽጉጥ ሌላኛ ፈጠራው ሲሆን፣ሽጉጡ ከመተኮስ ጉልበቱ ባሻገር ከታሪክ እና ከዘመን ጋር የተስማማ መሆኑ በታሪክ ባለሙያዎች ዘንድ ግርምትን ፈጥሯል፡፡

አቶ ዮናስ ይትባረክ ሽጉጡን የጎንደር ከተማ ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ተረክቦ ወደ ሙዚየም እንደገባ ገልፀውልናል፡፡
በየሺሀሳብ አበራ – አብመድ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram