fbpx

HT

ሐበሻ ታይምስ ሚዲያ

AMHARIC

አዲሱ “አንድሮይድ ፒ” ስማርት ስልካችንን እንደ ብሉቱዝ ኪቦርድና ማውዝ ማስጠቀም ይችላል ተባለ

ጎግል በቅርቡ ይፋ የሚያደርገው አዲሱ አንድሮይድ ፒ ኦፕሬቲንግ ሲስተም በርካታ አዳዲስ ነገሮችን ያካተተ መሆኑ ተነግሯል።

ከወራት በፊት ይፋ የተደረገው ኦፕሬቲንግ ሲስተሙ በመጪው ሳምንታት ውስጥ ተጠቃሚዎች ዘንድ መድረስ ይጀምራል ተብሎ ተጠብቋል።

አንድሮይድ ፒ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ከዚህ ቀደም ከተለቀቁት በተሻለ መልኩ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን አካቶ የሚመጣ መሆኑም ተጠቁሟል።

ከእነዚህም ውስጥ ስማርት ስልካሽንን በብሉቱዝ አማካኝነት ወደ ገመድ አልባ ኪቦርድ (መፃፊያ) እና ማውዝ መቀየር የሚችል መሆኑ ተነግሯል።

ይህም ስማርት ስልካችንን ከላፕቶፕ ኮምፒውተር፣ ዴስክ ቶፕ ኮምፒውተር ወይም ታብሌታችን ጋር በብሉቱዝ አማካኝነት በማገናኘት ጽሁፍ ለመፃፍ እና የተለያዩ ነገሮችን ለመጠቀም ያስችላል።

አዲሱን አንድሮይድ ፒ ቀድመው ያገኛሉ የተባሉት ስማርት ስልኮችም ጎግል ፒክስ እና ፒክስል 2 መሆናቸው ተነግሯል።

ምንጭ፦ www.techworm.net

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram