fbpx

አይጦች ከደቡብ ጆርጂያ የዱር እንሳት መኖሪያ በዘመቻ እንዲጠፉ ተደረገ

በደቡባዊ አትላንቲክ ደቡብ ጆርጂያ ደሴት የዱር እንስሳት መኖሪያ የሚገኙ አይጦች ችግር እየፈጠሩ በመሆናቸው በዘመቻ እንዲጠፉ ተደረገ።

አይጦቹ በአካባቢው ብቻ በሚገኙ የወፍ ዝርያዎች ላይ ጥቃት በመፈፀማቸው ነው በዘመቻ እንዲጠፉ የተደረገው።

ለዚህ ዘመቻ 10 ሚሊየን የብሪታንያ ፓውድ የተመደበ ሲሆን፥ ይህም በአካባቢው ያለውን የብዛህይወት መጠበቅ እንዳስቻለ ተነግሯል።

በበፈረንጆቹ 2010/11 በደሴቱ የባህር ዳርቻዎች በሶስት ደረጃዎች አይጦችን ማጥፋት ተጀምሮ እንደነበር ተብላል።

በወቅቱ አይጦችን የማጥፋት ስራው የተከናወነ ሲሆን፥ የማጥፋቱ ዘመቻ ያስገኘው ውጤት እና ያለበት ደረጃ ምርመራ ከሁለት አመታት መካሄዱ ታውቋል።

በዚህም መሰረት ስልጡን ውሾችን በመጠቀም የማጣራት ስራ በአካባቢው በማድረግ ስራ እንደተጠናቀቀ ተነግሯል።

ወጥመድ በማዘጋጀት እና በሌሎች መንገዶች በመጠቀም ተደረገው ምርምራ በአካባቢው አይጥ መኖር የሚያሳይ መረጃ እንዳልተገኘ ታውቋል።

ምንጭ፥ ቢቢሲ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram