አይነስውሩ ግለሰብ የአለም ረጅሙን የአሸዋ በርሃ ብቻውን ማቋረጥ ጀመረ

አልባር ቴሲኤራ የተባለው ፈረንሳዊ አይነስውር መምህር በቦሊቪያ የሚገኘውን 140 ኪሎ ሜትር የሚረዝመውን የአለም ረጂሙን የአሸዋ በርሃ ማቋረጥ መጀመሩ ተነገሯል።

ሳላር ዴ ኡዩኒ የተባለውን ይህ የአሸዋ በርሃ ግለሰቡ በትናትናው ዕለት ማቋረጥ የጀመረ ሲሆን፥ ሰባት ቀናት ይፈጅበታል ተብሏል።

በርሃው በ3 ሺህ 650 ሜትር ከፍታ ላይ እንደሚገኝና ከ3 እሰከ 20 ዲግሪ ሴሊሸስ የሚደርስ የሙቀት መጠን የሚዘገብበት አካባቢ እንደሆነ ተጠቁማል።

ግለሰቡ በፈረንሳይ አይነስውሩ ህፃናት መምህር ሲሆን፥ ላለፉት ሁለት ዓመት አይነስውራን ሰዎች አስገራሚ ጉዞ እንደሚያደርጉ ለማሳየት ሙከራ እያደረገ መቆየቱን አስታውቋል።

በዚህ ግለሰቡ በድምፅ የታገዘ የመንገድ መምሪያ(ጂፒኤስ)ና የድንገተኛ ቡድን በማካተት ይህ የአሸዋ በርሃ ለማቃረጥ መዘጋጀቱ ተነግሯል።

አልባር ቴሲኤራ የድንገተኛ ቡድን አባላት በርቀት እንዲከተሉትና ካልጠየቃቸው በስተቀር ምን አይነት ድጋፍ እንዳይሰጡት እንዳሳሰባቸው ተነግሯል።

አይነስውሩ ተጓዥ ጉዞን ፈታኝና ከባድ ለማድረግ በማሰብ ረጅሙ የበርሃውን መመረጡ ደግሞ ሌላ ግርምትን በሰዎች መፍጠሩ ተነግሯል።

ግለሰቡ የታሸገ የመጠጥ ውሃ፣ ፍራሽ እንዲሁም ሌሎች አስፈላጊ መሳሪያዎችን በመያዝ ጉዞውን እንደጀመረና በጉዞ ወቅት ችግር ቢፈጠር ድጋፍ የሚሰጡ ዶከተርና የድንገተኛ ቡድን አባላት ከኋላው ይከተላሉ ተብሏል።

ይህን የአሸዋ በርሃ በየቀኑ 20 ኪሎ ሜትሮችን በማቋረጥ ለማጠናቀቅ ጥረት እንደሚያደርግ የተጠቆመ ሲሆን፥ ይህን በርሃ ማቀረጥ የአካል ጉዳት ለሌለባቸው ሰዎችም እጅግ ፈታኝ እንደሆነ ይነገራል።

ምንጭ፦ ኦዲቲሴንትራል

Share your thoughts on this post

%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram