አይቢኤም የአለማችን እጅግ ትንሿን ኮምፒውተር ይፋ አድርጓል
አይቢኤም የአለማችን እጅግ ትንሿን ኮምፒውተር ይፋ አድርጓል
በቴክኖሎጂ ኩባንያው በአይቢኤም (IBM) ይፋ የሆነችው እጅግ ትንሿን ኮምፒውተር 1 ሚሊሜትር በአንድ ሚሊሜርት መጠን እንዳላት ታውቋል፡፡
ኮምፒውተሯም ፕሮሰስ የማድረግ አቅሟ ከቀድሞ የአይቢኤም ናይንታይስ ዴስክቶፕ ኮምፒውተር (Nineties IBM desktop computers) እኩል x86 ቺፕ (x 86 chips) እንዳላት ተነግሯል፡፡
ማይክሮስኮፒክ ክሪፕቶ አንከር ኮምፒውተሯ የተሟላ ሲስተም ያላት ሲሆን ከእነዚህ መካከልም በውስጧ ፐሮሰሰር ፣ ሚሞሬ፣ ስቶራጅ እና የኮሚኒዩኬሽን ሞጁል እንዲሁም ወሳኝ ጸረ- ማጭበርበር መሳሪያ እንዳላት ታውቋል፡፡
ኮምፒውተሯ ሙሉ ማብራሪያ በለላስ ቪጋስ በሚደረገው የ2018 ኮንፍርነስ ላይ ለማቅርብ ማሰቡን ኩባንያው ጠቅሷል፡፡
ምንጭ:- ኢንዲፐንደንት
Share your thoughts on this post