fbpx

አንድ ጊዜ በመውሰድ የወባ በሽታ አምጭ ጥገኛ ህዋስ ከሰውነት ውስጥ ለማጥፋት የሚያስችል ክኒን ይፋ ሆነ

ተመራማሪዎች አንድ ጊዜ በመውሰድ የወባ በሽታ አምጭ ጥገኛ ህዋስ ከሰውነት ውስጥ ለማጥፋት የሚያስችል ክኒን ይፋ አደረጉ።

መድሃኒቱ ባለፉት 60 ዓመታት አገልሎት ላይ ከዋሉት መድሃኒቶች በፈዋሽነቱ ቀዳሚው ነው ተብሏል።

ታፈኖኮን የተባለው አዲሱ የወባ በሽታ ክኒን ለወባ በሽታ መንስኤ የሆነውን ጥገኛ ህዋስ ከጉበት ውስጥ የሚያጠፋ ሲሆን፥ ከህመም ለማገገምና ሌሎች የህመም ስሜቶችን ለማስታገስ ከሌሎች መድሃኒቶች ጋር ጎን ለጎን የሚወሰድ እንደሆነ ነው የተገለጸው።

በአብዛኛው የአፍሪካ ሃገራት የወበባ በሽታ በዚህ የወባ በሽታ አምጭ ህዋስ የሚከሰት ሲሆን፥ ጥገኛ ህዋሱ በጉበት ውስጥ በመቀመጥ የሰውነት የመከላከል አቅም ሲዳከም በሽታው እንደገና በማገርሸት የሚከሰት መሆኑ ነው የተገለጸው።

በዓለም አቀፍ ደረጃ በየዓመቱ በዚሁ የወባ በሽታ ዓይነት 8ነጥብ5 ሚሊየን ያህል ሰዎች እንደሚያዙ ዘገባው ያስረዳል።

በተለይም ህፃናት አንዴ በዚሁ ጥገኛ ህዋስ ከተበከሉ በሽታው በተለያየ ጊዜ በማገርሸት ትምህርታቸውን ለመከታተል እንቅፋት እንደሚሆንባቸው ተመላክቷል።

የወባ ትንኞችም በቀላሉ ከእነዚህ ሰዎች ጥገኛ ህዋሱን ወደ ጤነኛ ሰወች እንደሚያዛምቱም በዘገባው ተጠቁሟል።

አዲሱን መድሃኒት አንድ ጊዜ በውሰድ ጥገኛ ህዋሱን ከጉበት ውስጥ ማጥፋት የሚቻል ሲሆን፥ የአሜሪካ የምግብና መድሃኒት ቁጥጥር ለዚሁ ክኒን እውቅና መስጠቱም ተገልጿል።

አዲሱን የወባ መድሃኒት ከሌሎችየወባ መከላከያዎች ዘዴዎች ጎን ለጎን መጠቀሙ የወባ በሽታ ተጋላጭነትን በከፍተኛ ደረጃ ይቀንሳል ተብሎ እምነት እንደ ተጣለበትም ነው ዘገባው የሚያመላክተው።

ምንጭ ፦ bbc.com

የተተረጎመው፦ በእንቻለው ታደሰ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram