fbpx

አንድ ዓይን ያለው በአፈር አይጫወትም! ተወልደ ተባረረ ከሚለው ማን ይተካዋል የሚለው ሊያሳስበን ይገባል

የአገራችን ለውጥ እየተፋጠነ አየር መንገዱን እያነቃነቀ መሆኑ እየተሰማ ነው። ወያኔ በጠመንጃ አስፈራርቶ ከያዘው የፖለቲካና የኢኮኖሚ ማማ ላይ እየተስፈነጠረ እየወደቀ ነው። በፖለቲካ ሹመት ከተያዙ ቁልፍ ቦታዎች አንዱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ነው። በሰው ሃይል አስተዳደርና በሙስና ክስ የሚቀርብበት አቶ ተወልደ እየር መንገዱን ከአቶ ግርማ ዋቄ ተረክቦ ማሳደጉን ግን መካድ አይቻልም።

ለማንኛውም ሰሞኑን በየሚዲያው የአየር መንገድ ሃላፊዎች ችግር ተጋነው መወራታቸው የሰውዬው እህል ውሃ ማብቃቱን ይጠቁማል። ሰውዬው መባረሩ ተገቢ ነው ቢባል እንኳን ተተኪው ስራ አስፈፃሚ ማን ይሆናል የሚለው ጥያቄ እጅግ ያሳስባል። በፌስቡክ የተወራው ሁሉ ባይታመንም ወ/ሮ ሙሉ የተባለች ሴትዮዋ ተተኪ ስራ አስፈፃሚ እንደምትሆን ሲወራ ከርሟል። በእርግጥ እንደተወራው ይህችን ሴትዮዋ ከሾሙ አብደዋል ማለት ነው።

አቭዬሽን ኢንደስትሪ የማያውቅ ሰው ለኢትዮጵያ አየር መንገድ መሾም ድርጅቱን በጥቂት አመት ወደ ተረት ሊለውጠው ይችላል። ድርጅቱን ባይጥለውም እንኳን የሚፈለግበት ደረጃ እንዳይደርስ ግን እንቅፋት መሆኑ አይቀርም። አንድ አይና በአፈር አይጫወትም እንዲሉ አየር መንገዳችንን በፖለቲካ ሹመት ለመምራት መሞከር አሳፋሪ ነው። አምባገነኑ መንግስቱ ሃይለማርያም በአየር መንገድ ምደባ አልቀለደም፣ ዘረኛው መለስ ዜናዊ ትግሬ ሰራተኛ አሰልጥኖ ለመመደብ ከ15 አመት በላይ መጠበቅ ነበረበት እንጂ ከበረሃ አንስቶ አልመደበም። ጠ/ሚ አብይ በብሄርና ፆታ ተዋስኦ መመደብ ከፈለገ የአቭዬሽን እውቀት ያላቸው ሌሎች ኢትዮጵያውያን ፈልጎ መመደብ ይችላል።

ወ/ሮ ሙሉ ከዘሪቱ ጋር ፊልም ስትሰራ አይቻታለሁ። ሴትዮዋን መመደብ የግድ ከሆነ ብሔሬዊ ትያትር ቤት ብትገባ ይስማማታል። ወንድም ይሁን ሴት የአየር መንገድ ስራ እውቀት የሌለው ሰው መመደብ ታላቅ ጥፋት ነው። መለስ ዜናዊ በማን አለብኝነት ከበረሃ የመጡ ታጋዮችን ሜቴክ የሚባል የቴክኖሎጂና ምህንድስና ድርጅት ውስጥ የበላይ አድርጎ ሾሞ በሕዝብ ሃብትና በብሄራዊ ፕሮጄክት ላይ መቀለዳቸው ከህሊናቸው አልጠፋም። አየር መንገዳችን የብሄርና የፆታ ፖለቲከኞች ኮታ ማሟያ መሆን የለበትም። አቅምና ብቃት ያለው ተተኪ ስራ አስፈፃሚ የግድ ሴት ወይም ሌላ ብሄር ያለው መሆን የለበትም። በፆታ ወንድ ቢሆንም ወይንም በብሄር ትግሬ ቢሆን ብቃቱ ካለው ይሾም። ካለበለዚያ ግን አየር መንገዳችን ባይወድቅ እንኳን የሚደርስበት ከፍታ ላይ ግን አይደርስም።

ልብ ያለው ልብ ይበል!

(ዮና ቢር)

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram