fbpx

አነስተኛ ገቢ ያላቸው የመንግስት ሰራተኞችን ተጠቃሚ የሚያደርገው 5ሺ የጋራ መኖሪያ ቤቶች እጣ ወጣ

አነስተኛ ገቢ ያላቸው የመንግስት ሰራተኞችን ተጠቃሚ የሚያደርገው 5ሺ የጋራ መኖሪያ ቤቶች እጣ በዛሬው እለት ወጥቷል።

የእጣ አወጣጡ ስነስርአት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ድርባ ኩማ በተገኙበት ነው በዛሬው እለት የተካሄደው።

በእጣ ማውጣቱ ላይ የተገኙት ከንቲባ ድሪባ ኩማ፥ ከ176 ሺህ በላይ ቤቶችን እስካሁን ለተጠቃሚ ያስተላለፈው የከተማው አስተዳደር አሁንም ከ132 ሺህ በላይ ቤቶችን በግንባታ ላይ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል።

በተጨማሪም ከፍለው መውሰድ ለማይችሉ ዜጎች ደግሞ መንግስት 1 ሺህ 700 በላይ ቤቶች በ2 ሳይቶች ለኪራይ እያዘጋጀ መሆኑንም ተናግረዋል።

እጣ የወጣባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶቹ 10/90 ሲሆኑ የከተማ አስተዳደሩ በ400 ሚሊየን ብር ከቤቶች ልማት ኤጀንሲ የገዛቸው ናቸው።

በዕጣ ስነስርዓቱ ላይ በመንግስት ከሚከፈለው አነስተኛ ክፍያ እስከ 3ሺ 500 ብር የወር ገቢ ያላቸው የመንግስት ሠራተኞች እና ኑሮን መቋቋም የማይችሉ 5ሺ የመንግስት ሰራተኞች ተጠቃሚ ይሆናሉ።

የቤቶቹም ኪራየ ዋጋ 315 መሆኑ በስነስርዓቱ ላይ ተጠቅሷል።

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram