fbpx

HT

ሐበሻ ታይምስ ሚዲያ

AMHARIC

አቶ ኢሳያስ ጅራ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ሆነው ተመረጡ

አቶ ኢሳያስ ጂራ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ባካሄደው ሁለተኛው ዙር ምርጫ ፕሬዚዳንት ሆነው ተመረጡ።

ዛሬ ለሁለተኛ ጊዜ በተካሄደው ምርጫ አቶ ኢሳያስ 87 ድምፅ በማግኘት ነው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ሆነው የተመረጡት።

ከአቶ ኢሳያስ ጋር የተወዳደሩት አቶ ተካ አስፋው ሲሆኑ፥ 58 ድምፅ በማግኘት ሁለተኛ ሁነዋል።

ከምሳ ሰዓት በፊት በተካሄድው የፕሬዚዳንት ምርጫ አቶ ኢሳያስ ጂራ 66 ድምፅ በማግኘት የተመረጡ ቢሆንም የፊፋው ተወካይ ፕሬዚዳንት ሆኖ የሚመረጠው ከ145 ድምፅ 50 ሲደመር አንድ በመቶ ማግኘት አለበት በማለታቸው ነው እንደገና እንዲካሄድ ፌዴሬሽኑ የወሰነው።

ከዚህ ምርጫ አቶ ጁነዲን ባሻ እና አቶ ተስፋየ እራሳቸውን በማግለላቸው ምርጫው የተካሄደው በአቶ ኢሳያስ ጂራ እና አቶ ተካ አስፋው መካከል ነው።

ቀደም ሲል በተካሄደው ምርጫ ከኦሮሚያ የተወከሉት አቶ ኢሳያስ ከ145 ደምፅ ውስጥ 66 ድምፅ በማግኘት የቻሉ ሲሆን፥ አቶ ተካ አስፋው 47 እና አቶ ጁነዲን ባሻ 28 ድምፅ ማግኘታቸው ይታወሳል።

ኤፍ.ቢ.ሲ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram