fbpx

አትክልትን አዘውትሮ መመገብ ለምን ያስፈልጋል?

አትክልትን አዘውትሮ መመገብ ጤናማ ሆኖ ለመኖር ከሚያስችሉ ነገሮች መካከል በዋነነት ይጠቀሳል።


ይህም ያስፈለገበት ሰዎች አትክልት በሚመገቡነት ወቅት በቀላሉ ሰውነታቸው ፋይበር፣ ፎሊክ አሲድ እና ቫይታሚኖችን ማግኘት የሚያስችል በመሆኑ ነው።

ሰዎቸ አትክልትን አዘውትረው ሲመገቡ የኮሌስትሮል መጠናቸው ዝቅተኛ እንደሚሆን እና የድም ግፊታቸውን እንደሚቀንስ መረጃዎች ያመለከታሉ።

በመሆኑም በዛሬው የጤና አምድ ከላይ እንደተጠቀሰው ሰዎች ጤናማ ህይወት እንዲመሩ የሚያስችለው አትክልት ያለውን ጠቀሜታ በተወሰነ መልኩ ይቀርባል።

1. የደም ግፊትን ዝቅተኛ ያደርጋል

በተለያዩ ጊዜያት የተካሄዱ ጥናቶ እንደሚያመለክቱት አትክልት የደም ግፊትን ዝቅተኛ እንዲሆን ከማድረግ በተጨማሪ የደም ግፊትን ዝቅ ለማድረግና ለመቆጣጠር ይረዳል።

2. የተረጋጋ ስሜት እንዲኖር ያስችላል

ስጋን፣ አሳን እንዲሁም አትክልትና አረንጓዴ ምግቦችን አዘውትረው በሚመገቡ ሰዎች የተካሄደ ጥናት እንደሚያመለክተው አትክልትን አዘውተረው የሚመገቡ ሰዎች የተረጋጋና የተሻለ ስሜት እንዳላቸው አመልክቷል።

3. ረጅም እድሜን ለመኖር

የአትክልት ምግቦች የሰዎች የመኖሪያ እድሜን 20 በመቶ ክፍ እንደሚያደርጉ መረጃዎች ያመለክተታሉ። ጥናቶቹ እንደሚያመለክቱት ስጋ በተደጋጋሚ የሚመገቡ ሰዎች ረጅም እድሜ እንደማይኖሩና አድሜያቸው እየገፋ በሚሄድበት ወቅት ለተለያዩ የአካል ጉዳቶች እንደሚጋለጡ ይነገራል።

ከዚህ በተጨማሪ በሸታ የመከላከል አቅምን እንደሚቀንስ እና የሰውነት ሀይል በቂ እንዳይሆን በማድረግ ችግር እንደሚፈጥር ነው የተጠቆመው።

አትክልትን አዘውተሮ መመገብ ግን ጤናማ ህይወትን በመምራት ረጅም እድሜ ለመኖር የሚያስችል ሲሆን፥ ለዚህም በጃፓን የሚገኙ እና አብዛህኛው ምግባቸው አትክልት የሆነ ማሀበረሰብ ተጠቅሰዋል።

4. የስኳር በሽታ ተጋላጭነትን መቀነስ ያስችላል

አትክልትን መመገብ ምንም እንኳ የስኳር በሽታን መፈወስ ባይችልም ሰዎች ለበሽታው ያላቸውን ተጋላጭነት እንደሚቀንሰው ነው የተጠቆመው።

ከዚህ ባለፈ በደም ውስጥ የሚገኝ የስካር መጠን ለመቆጣጠርና በበሽታው የተጠቁ ሰዎች በመልካም ጤንነት ላይ መቆየት እንዲቸሉ ከፍተኛ የሆነ ጠቀሜታ አለው ተብሏል።

5. የኮሌስትሮል መጠንን ዝቅ ያደርጋል

ከምግብ መዓደ ስጋን እና ከፍተኛ የስብ መጠን ያላቸው ምግቦችና በማራቅ እና አትክልትን በማዝወተር በሰውነት ውስጥ ያለን የኮሌስትሮል መጠን ዝቅ ያደርጋል።

6. አጥንት ጥንካሬ እንዲኖረው ያሰችሏል

አትክልትና አረንጓዴ ምግቦችን ማዘውተር ከተጠቀሱት ጥቅሞች በተጨማሪ በሰውነት ውስጥ የሚገኝ ካልሽየም መጠን በማሳደግ አጥንት ጥንካሬ እንዲኖረው ይረዳል።

ከእነዚህ ጠቀሜታዎች በተጨማሪ አትክልትን ማዘውተር ከምግብ ጋር ተያይዘው የሚከሰቱ በሽታዎችን ለመቀነስ ፣ ሰውነት ሀይል እንዲያገኝ፣ ለስትሮክ፣ ከልክ ላለፈ ውፍረት እንዲሁም ሰዎች ለሌሎች በሽታዎች ያላቸውን ተጋላጭነት ለመቀነስ ይጠቅማል።

ምንጭ፦ ግሎባልሄሊንግ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram