አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ የግሬት ማንቸስተር 10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫን አሸነፈች

አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ በዛሬው እለት በእንግሊዟ ማንችስተር የተካሄደውን የግሬት ማንቸስተር 10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫን አሸነፈች።

አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ 10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድሩን በ31 ደቂቃ ከ08 ሰከንድ በመግባት ነው በአንደኝነት ያጠናቀቀችው።

ጥሩነሽን በመከተልም ኬንያዊቷ ጆይስሊን ጆፕጎስኪ በ31 ደቂቃ ከ57 ሰከን ሁለተኛ ስትወጣ፤ ቤትሲይ ሲያና ደግሞ በ32 ደቂቃ ከ25 ሰከንድ ሶስተኛ ወጥታለች።

በወንዶች በተካሄደው ውድድር ደግሞ እንግሊዛዊው አትሌት ሞ ፋራህ ውድድሩን በ28 ደቂቃ ከ27 ሰከንድ በመግባት በአንደኝነት ማጠናቀቅ ችሏል።

farah.jpg

ኡጋንዳዊው ሞሰስ ኪፕሪሮ ከሞህ ፋራህ በአንድ ሰከንድ ብቻ ወደ ኋላ በመቅረት በ28 ከ28 ሰከንድ በመግባት ውደድሩን በሁለትኘት አጠናቋል።

ኬንያዊው አቤል ኪሩይ ደግሞ 28 ደቂሰሰ 52 ሰከንድ በመግባት 3ኛ ሆኖ አጠናቋል።

Share your thoughts on this post

%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram