fbpx

አትሌት ጌታነህ ሞላና ማሚቱ ዳስካ በኮሎራዶ የተካሄደ የ10 ኪ.ሜ የጎዳና ላይ ሩጫ አሸነፉ

ኢትዮጵያውያኑ አትሌት ጌታነህ ሞላ እና ማሚቱ ዳስካ በአሜሪካዋ ኮሎራዶ የተካሄደውን የቦልደር ባውልደር መታሰቢያ የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ አሸንፈዋል።

በወንዶች የተካሄደውን ውድድር ኢትዮጵያዊው አትሌት ጌታነህ ሞላ 28 ደቂቃ፣ ከ18 ሰከንድ በመግባት ነው አንደኛ በመሆን ያጠናቀቀው።

ታንዛኒያዊው አትሌት በጋብሬል ጊያይ በ28 ደቂቃ ከ39 ሰከንድ 2ኛ በመሆን ውድድሩን ሲያጠናቅቅ፤ ባህሬናዊው አትሌት ሀሳን ኤልአባሲ 28 ደቂቃ ከ44 ሰከንድ በመግባት ውድድሩን በ3ኛ ነት አጠናቋል።

ኢትዮጵያዊው አትሌት ሌሊሳ ዴሲሳ 28 ደቂቃ ከ54 ሰከንድ በመግባት ውድድሩን በ4ኛነት ያጠናቀቀ ሲሆን፥ ለባህሬን የሚሮጠው አትሌት አወቀ አያሌው በ28 ደቂቃ ከ57 ሰከንድ በመግት 5ኛ ደረጃን ይዟል።

በሴቶች በተካሄደው ውድድር ደግሞ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ማሚቱ ዳክሳ 32 ደቂቃ፣ ከ36 ሰከንድ በመግባት ነው የ10 ኪሎ ሜትር ውድድሩን አንደኝነት ያጠናቀቀችው።

አሜሪካዊቷ አትሌት አለፋይን ቱሊያሙክ 2ኛ ደረጃን ስትይዝ፤ ኢትዮጵያውያኑ አትሌቶች እታገኝ ወልዱ እና ህይወት አያሌው 3ኛ እና 4ኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን አጠናቀዋል።

ምንጭ፦ African Athletics United

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram