fbpx

አስምና ሌሎች የመተንፈሻ አካል የጤና እክሎችን ለመከላከል የሚመከሩ አመጋገቦች…

ተመራማሪዎች በቅርቡ ባወጡት የጥናት ውጤት አስምና ሌሎች ከመተንፈሻ አካላት ጋር ተያይዘው የሚከሰቱ በሽታዎችን አመጋገብ በማስተካከል መከላከል እንደሚቻል አስታውቀዋል።

እንደ ተመራማሪዎቹ ገለጻ አትክልትና ፍራ ፍሬዎችን አዘውትረን የምንመገብ ከሆነ ለአስም እና መሰል የመተንፈሻ አካል የጤና እክል የመጋለጥ እድላችን አነስተኛ ይሆናል።

ለአስም እና መሰል የመተንፈሻ አካል የጤና እክል ቀድመን የተጋለጥን ቢሆን እንኳ አትክልትና ፍራፍሬን አዘውትሮ መመገብ ህመሙ የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ ይረዳናል ነው ያሉት ተመራማሪዎቹ።

በአትክልት እና ፍራፍሬ ውስጥ የሚገኙ አንቲኦክሲደንት እና አንቲ ኢንፍላማቶሪ ንጥረ ነገሮች ሰዎች ለመተንፈሻ አካል ችግር እንዳይጋለጡ ይከላከላሉም ብለዋል ተመራማሪዎቹ።

ተመራማሪዎቹ አክለውም ስጋ አብዝቶ መመገብ እንዲሁም ጨው እና ጣፋጭነት የሚበዛባቸውን ምግቦችን መመገብ የአስም በሽታ መከላከልን አስቸጋሪ ያደርጋለም ብለዋል።

ጥናቱ በፈረንሳይ ተመራማሪዎች የተካሄደ ሲሆን፥ በጥናቱ ላይም ከ35 በላይ ሰዎች ተሳትፈዋል።

ተመራማሪዎቹ በጥናቱ ላይ የተካፈሉትን ሰዎች የአመጋገብ ስርዓት እና አመጋገባቸው ከአስም በሽታ እና ሌሎች የመተንፈሻ አካላት እክል ተጋላጭነት ላይ ያለውን ተጽዕኖም ተመልክተዋል።

በዚህም ጤናማ የተባለና አትክልትና ፍራፍሬን በአመጋገባቸው ውስጥ አካተው የሚመገቡ ወንዶች እንደ አስም ላሉ የመተንፈሻ አካል የጤና እክል የመጋለጥ እድላቸው በ30 በመቶ ቀንሶ ተገኝቷል።

አትክልትና ፍራፍሬን በአመጋገባቸው ውስጥ አካተው የሚመገቡ ሴቶች ደግሞ እንደ አስም ላሉ የመተንፈሻ አካል የጤና እክል የመጋለጥ እድላቸው በ20 በመቶ ቀንሶ ተገኝቷል።

ቀድሞውኑ በአስም እና በሌላ የመተንፈሻ አካል የጤና ችግር የተጋለጡ ላይ በተደረገው ጥናት ደግሞ ጤናማ አመጋገብን የሚከተሉ ወንዶች በበሽታው ሳቢያ የሚደርስባቸው ጉዳት በ60 በመቶ ቀንሶ ተገኝቷል።

ጤናማ አመጋገብን የሚከተሎ ሴቶች ደግሞ በበሽታው ሳቢያ የሚደርስባቸው ጉዳት በ27 በመቶ ቀንሶ መገኘቱንም ነው ተመራማሪዎቹ የገለጹት።

ከፓሪስ 13 ዩኒቨርሲቲ እና ከፈረንሳይ የጤና ኢኒስቲቲዩት የተውጣጡት ተመራማሪዎቹ በአስም እና በአመጋገብ ስርዓት መካከል ታለው ግንኙት ላይ አሁንም ቀሪ ጥናቶች አሉ፤ አሁን የተሰራው ብቻ በቂ አይደለም ብለዋል።

ሆኖም ግን በጥናቱ በተገኘው ውጤት መሰረት ጤናማ የሆነ አመጋገብን መከተል ለአስም እና ሌሎች ከመተንፈሻ አካል ጋር የተያያዙ የጤና ችግሮችን ለመከላከል እንደሚረዳ ነው ተመራማሪዎቹ ያስታወቁት።

ምንጭ፦ www.dailymail.co.uk

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram