አሳዛኝ ዜና – የአቶ ግርማ ዘለቀ (ስንዝሮ) የቀብር ስነ ስርዓት በባህርዳር ከተማ ተፈጸመ
አሳዛኝ ዜና – የአቶ ግርማ ዘለቀ (ስንዝሮ) የቀብር ስነ ስርዓት በባህርዳር ከተማ በአባይ ማዶ ገብርዔል ቤተክርስቲያን ዛሬ ከቀኑ 6 ሰዓት ተፈጽሟል፡፡
በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነውን አኒሜሽን ስንዝሮን የሰሩትና ያስተዋወቁት አቶ ግርማ ዘለቀ ሥመ ጥር ባለሙያ ነበሩ፡፡
ኑሯቸውን በአሜሪካ አድርገው ከቆዩ በኋላ ወደ ትውልድ ሃገራቸው ባህርዳር ዘመድ ለመጠየቅ ባመሩበት ሰዓት ድንገት በእህታቸው ልጅ በተደጋጋሚ በቢላ ተወግተው ወደ ሆስፒታል ያመራሉ፡፡
በፈለገ ሕይወት ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል አንድ ሳምንት በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ትናንት ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ያርፋሉ፡፡
የመጀመሪያውን የቢልቦርድ ማስታወቂያ ለሃገራችን ያስተዋወቁት የ63 ዓመቱ አቶ ግርማ ዘለቀ (ስንዝሮ) ባለትዳርና የአራት ልጆች፤ (የአንድ ወንድ እና የሦስት ሴቶች) አባት ነበሩ::
Share your thoughts on this post