አራት የፍትሐብሄር ህጎች ላይ ማሻሻያ ሊደረግ ነው
(ኤፍ.ቢ.ሲ) ለ58 ዓመታት ሲሰራባቸው የቆዩ አራት የፍትሐብሄር ህጎች ላይ ማሻሻያ ሊደረግ መሆኑ ተገለፀ።
የኢፌዴሪ የፍትህና የህግ ምርምርና ስልጠና ኢንስቲትዩት እንዳስታወቀው፥ ባለፉት 8 ወራት በህጎቹ ላይ የማሻሻያ ጥናት ሲያደር ቆይቷል።
ኢንስቲትዩቱ በዛሬው እለት ይፋ እንዳደረገውም ፥ ማሻሻያ የሚደረግባቸው የንብረት፣ የሰዎች፣ የውል እና የውርስ ህግ ላይ ነው።
የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዳይሬክተር አቶ ተስፋለም ይህደጎ እንዳሉት፥ ህጎቹን ማሻሻል ያስፈለገው ወቅቱ ከሚፈልገው የቴክኖሎጂ ስርዓት ጋር ባለመጣጣማቸው ነው።
እንዲሁም ለዳኞች ውሳኔ አሻሚ የሆኑና ጥያቄ የሚያስነሱ ድንጋጌዎችን የያዙ በመሆናቸው ነው ሲሉም ዳይሬክተር አቶ ተስፋለም ተናግረዋል።
የማሻሻያ ጥናቱ በሚቀጥሉት 4 ወራት እንደሚጠናቀቅና ውጤቱ ለሚመለከተው የህግ አርቃቂ አካል በዚሁ ዓመት የሚቀርብ መሆኑ ተገልጿል።
በዙፋን ካሳሁን
Share your thoughts on this post